Loading
Singer
ተኩላው ፡ ለምድ ፡ ለብሶ ፡ እውነትን ፡ አለባብሶ ሲዖል ፡ እንዳይከትህ ፡ ንቃ ፡ በል ፡ ወገኔ ፡ አስተውል አምልጥ ፡ ከጠላትህ ፡ ወዳጅ ፡ መስሎ ፡ ሳይገድልህ በጉብዝናህ ፡ ወራት ፡ አምላክህን ፡ አስብ ፡ ፈጣሪህን መዳን ፡ በሌላ ፡ የለም ፡ አትታለል ፡ ወገኔ እዳህን ፡ የከፈለው ፡ ይልሃል ፡ ና ፡ ወደኔ ከሞት ፡ መንገድ ፡ ተመለስ ፡ ኋላ ፡ ሳያጠፋህ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ከሲዖል ፡ ከሞት ፡ የሚያድንህ ሃብትህ ፡ ሞልቶ ፡ ቢትረፈረፍ ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ ፡ ቢበቃ ዝናህ ፡ ከአጥናፍ ፡ አጥናፍ ፡ ቢደርስ ፡ ለጊዜውም ፡ ቢያስመካህ ስልጣን ፡ ዕውቀትም ፡ ቢኖርህ ፡ የነገሥታት ፡ ዘር ፡ ብትሆን ዋስትናህ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለነፍስህ ፡ ቤዛ ፡ የሚሆን አዝ፦ ቤዛህ ፡ ቤዛህ ፡ ቤዛህ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፬x) የሚደግፍህ ፡ የሌለ ፡ ብትሆንም ፡ ችግረኛ ተስፋ ፡ ቆርጠህ ፡ የምትባዝን ፡ ያለምንም ፡ መጽናኛ ለጥያቄዎችህ ፡ ሁሉ ፡ መልስ ፡ የሚሆን ፡ በእውነት ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በደጅህ ፡ ነው ፡ በርህን ፡ ክፈትለት አስቀድመህ ፡ ከሁሉ ፡ አምላክህን ፡ ውደድ እንዲያሳይህ ፡ በጸጋው ፡ የሕይወትን ፡ መንገድ እሺ ፡ ብትል ፡ ለጌታ ፡ ብትታዘዝ ፡ ለቃሉ በበረከት ፡ ይሞላል ፡ የጐደለህ ፡ በሙሉ