Loading
Singer
አዝ፦ ቤተክርስቲያን ፡ ሙሽራይቱ ሙሽራሽ ፡ ሊመጣ ፡ ጊዜው ፡ አይደለም ፡ ወይ አጊጠሽ ፡ ጠብቂ ፡ ተዘጋጂ ፡ ቶሎ ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ መላዕክት ፡ አስከትሎ በመላዕክት ፡ ታጅቦ ፡ ኦሆ የቀድሞ ፡ ፍቅርሽን ፡ አድሺ ፡ በጊዜ ከአንቺ ፡ ይወገዱ ፡ ድካም ፡ ድንዛዜ ንቂ ፡ መብራት ፡ አብሪ ፡ ተዘጋጂ ፡ ፈጥነሽ ጠብቂው ፡ ኢየሱስን ፡ ጌጠኛ ፡ ልብስ ፡ ለብሰሽ ያማረ ፡ ልብስ ፡ ለብሰሽ ፡ አዎ በራድ ፡ ወይም ፡ ትኩስ ፡ ከቶም ፡ አይደለሽ እስካሁን ፡ ኖረሻል ፡ እንዲያው ፡ ለብ ፡ ብለሽ ትምክህትሽን ፡ ጣዪ ፡ አትበይ ፡ ሁሉ ፡ አለኝ ኋላ ፡ እንዳታጪ ፡ ሊመጣ ፡ ያለውን ሊገለጥ ፡ ያለውን ፡ አዎ አዝ፦ ቤተክርስቲያን ፡ ሙሽራይቱ ሙሽራሽ ፡ ሊመጣ ፡ ጊዜው ፡ አይደለም ፡ ወይ አጊጠሽ ፡ ጠብቂ ፡ ተዘጋጂ ፡ ቶሎ ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ መላዕክት ፡ አስከትሎ በመላዕክት ፡ ታጅቦ ፡ ኦሆ በፈሰሰልሽ ፡ ደም ፡ ጉድፍሽኝ ፡ አጥሪ ቀን ፡ ሳለ ፡ በጊዜ ፡ ራስሽን ፡ መርምሪ ኩል ፡ ግዢ ፡ ከጌታ ፡ ዓይንሽ ፡ ይከፈታል የጐደለሽ ፡ ሁሉ ፡ ያኔ ፡ ይታይሻል ያኔ ፡ ይታይሻል ፡ አዎ ኩራዝሽን ፡ አብሪ ፡ ዘይቱንም ፡ ግዢ ምንም ፡ እንዳይጐድልሽ ፡ ትጊ ፡ ተጠንቀቂ የምትጠብቂው ፡ ሙሽራ ፡ ይመጣል አታፍሪም ፡ ዘለዓለም ፡ እርሱም ፡ ያከብርሻል ከፍም ፡ ያደርግሻል ፡ አዎ ድል ፡ ለነሣው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ በዙፋን ፡ ላይ ፡ ይቀመጥ ፡ ዘንድ ፡ ይሰጠዋል መንፈስ ፡ ለአብያተ ፡ ክርስቲያናት ፡ የሚለውን ፡ ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ [1]