Loading
Singer
አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ ድንጋዩ ፡ እንዳይታይ ፡ በዝግባ ፡ ሲለበጥ ዝግባው ፡ ባማረ ፡ ወርቅ ፡ ሲያጌጥ መስራትም ፡ መሰራትም ፡ ያኔ ፡ ነበረ ይታያልም ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ ድንጋይ ፡ በድንጋይ ፡ ላይ ፡ ይፈርሳ ፡ ተባለ መች ፡ ቀረ ፡ ይኸው ፡ አሁን ፡ ሆነ ወንድም ፡ ከወንድሙ ፡ ጋራ ፡ ሳይጣበቅ ፡ በጩኸት ፡ ሞቀ ፡ ቤቱ ፡ ጋለ አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ ዘሩ ፡ በመንገድ ፡ ዳር ፡ ወድቆ ፡ ሲለቀም በጭንጫ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ ሲከስም ግማሹ ፡ በእሾህ ፡ መሃል ፡ ሲታነቅ ባለ ፡ ፍሬ ፡ ጠፍቶ ፡ ሲደርቅ ከወርቅ ፡ ይልቅ ፡ የሚፈተነው ፡ እምነት ፡ በዝማሬ ፡ ተመስሎ ፡ ጠፋ ከነኣን ፡ ላይገባ ፡ በኢያሪኮ ፡ ዙሪያ ፡ ሞልቷል ፡ መለከት ፡ የሚነፋ አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ እርስ ፡ በእርሳቸው ፡ የማይገላመጡ ለእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ሚሮጡ አገልጋዮች ፡ የሉም ፡ ራሳቸውን ፡ የካዱ ፡ ማይነቀፉ ፡ የተለወጡ ፍርድን ፡ ከራሱ ፡ ቤት ፡ ይጀምራልና ፡ ወደ ፡ ህያው ፡ ድንጋይ ፡ እናቅና በታቦት ፡ ብቻ ፡ እልልታን ፡ ከማቅለጥ ኢየሱስን ፡ እንምሰል ፡ እንደግ አዝ፦ ቤትህ ፡ በተሰራ ፡ ጊዜ ፡ የድንጋይ ፡ ጩኸት ፡ አልነበረም መራጃው ፡ ከቶ ፡ አልተንኳኳም በተሸለሙ ፡ ድንጋዮች ፡ የተሰራ ማን ፡ ታወከ ፡ መች ፡ ሆነ ፡ ተራራ ዛሬ ፡ ግን ፡ ያለመረዳት ፡ እሩጫ ፡ ሆነ በሰባራ ፡ ገል ፡ ቤትህ ፡ ተሰራ ፡ ተከናወነ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ ጩኸቱ ፡ ሲበዛ አውቄህ ፡ ልኑር ፡ ሰብስበኝ ፡ በቃልህ ፡ ጣዛ ኡ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁ ፡ የኔ ፡ ጌታ እራሴን ፡ ልየው ፡ ከጠዋት ፡ እስከማታ