Loading
ባማረ ፡ ባጌጠ ፡ ቤት ፡ ውስጥ ፡ ተሰይሚያለሁ በተዋበ ፡ ህዝብ ፡ ተከብቢያለሁ ዙሪያዬን ፡ የማየው ፡ ሁሉ ፡ ለዓይን ፡ ይስባል እኔ ፡ ግን ፡ ታምሜ ፡ ውበቴ ፡ ጠፍቶኛል ከቤትህ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ እኔ ፡ ጐድያለሁ ለሚያየኝ ፡ ለስሙ ፡ እኔ ፡ እንዳለሁ ፡ አለሁ ቤትህን ፡ ሲሞላው ፡ ዕልልታና ፡ ሆታ እኔን ፡ የሚያውከኝ ፡ የነፍሴ ፡ ጭንቀቷ የአንተ ፡ ቤት ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የእኔ ፡ ቤት ፡ ሌላ ፡ ነው ቤተ ፡ ሰሪው ፡ በዝቶ ፡ መላ ፡ የሚለኝ ፡ ማነው ቀርበህ ፡ ሳለህ ፡ ከደጅ ፡ ልትመጣ ፡ ወዳጄ እንዴት ፡ ይሆን ፡ የማይህ ፡ እሩቅ ፡ አገር ፡ ሄጄ ያዳራሹ ፡ ውበት ፡ እኔን ፡ ሸፍኖኛል ግዑዝ ፡ ከእኔ ፡ በልጦ ፡ አልፎ ፡ ይኮንነኛል በጌጥ ፡ የታጀበ ፡ ቤቱ ፡ ተሰርቶ ፡ አልቆ ልብ ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔን ፡ ቦታ ፡ ወስዶ ይበል ፡ እርሱም ፡ ይመር ፡ ቦታም ፡ አይጥበበን ግን ፡ ለታደሰ ፡ ቤት ፡ ምነው ፡ አጉል ፡ አጉል ፡ ሆነ እኔ ፡ ካልተደስኩኝ ፡ ካልሆንኩኝ ፡ እንደ ፡ ቤቱ ትርጉም ፡ የለሽ ፡ ኑሮ ፡ ድካም ፡ ነው ፡ ለከንቱ ቀኑ ፡ ቀርቧል ፡ እያልን ፡ ፍጻሜ ፡ የዘመን ከንቱ ፡ ቤት ፡ ስንሰራ ፡ ዘለዓለሙን ፡ ትተን ተላልፈን ፡ እንዳንቀር ፡ አቤቱ ፡ አደራ የተጣልን ፡ እንዳንሆን ፡ እንደነበርን ፡ ሥምህን ፡ ስንጠራ ሥምህን ፡ ስንተጠራ ፡ ሥምህን አደራ ፡ የነበርን ሥምህን ፡ ስንጠራ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.