Loading
Singer
ቤት ፡ አለኝ ፡ ቤት ፡ አለኝ ፡ ቤት (፪x) ስገባበት ፡ ኦሆ ፡ እርፍ ፡ ምልበት በሰማይ ፡ አለኝ ፡ ቤት አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ የሰው ፡ እጅ ፡ ጭራሽ ፡ ያልነካው ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ የሆነው አምላኬ ፡ እራሱ ፡ የገነባው የምድር ፡ ሃብት ፡ ቢከማች ፡ የማይተካው አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ ችግርን ፡ የማላይበት ሃዘን ፡ ለቅሶ ፡ ከቶ ፡ የሌለበት አምላኬ ፡ ሚመለክበት ዘለዓለም ፡ እኔም ፡ ማርፍበት አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ ምንኛ ፡ እድለኛ ፡ ነኝ የእግዚአብሔር ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ ነኝ አልሰጋም ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ ዋስትና ፡ ስላለኝ ፡ ብዬ አዝ:- የሰማዩን ፡ ቤቴን ፡ ሳስበው ይገርመኛል ፡ እደነቃለሁ እንደምድሩ ፡ አላፊ ፡ አይደለ ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ እጅግ ፡ ያማረ ና ፡ ኢየሱስዬ ፡ ናልኝ ና ፡ ኢየሱስዬ ፡ ና ፡ ናልኝ በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ (፪x) በጣም ፡ ናፈቅከኝ ፡ እጅግ ፡ ናፈቅከኝ (፪x)