Loading
Singer
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×) ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለ ፡ የህይወት ፡ ቃል ሌላ ፡ ስፍራ ፡ የትም ፡ 'ማላገኘው ብር ፡ የማይሰጠኝ ፡ ወርቅ ፡ የማይሰጠኝ የሕይወቴን ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠው፤ የሁልጊዜ ፡ ነው ፡ የልቤ ፡ ሰላም ከመንፈስህ ፡ ከቃልህ ፡ የመነጨው በዚህ ፡ አለም ፡ ነገር ፡ የማይወሰን የእኔን ፡ ሕይወት ፡ የደስታ ፡ ያደረገው ብዙ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ ብዙ ደስታ አለ፤ ብዙ ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ በሕይወቴ ብዙ ሰላም አለ፤ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ስላለ ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ ሸክም ፡ የከበደው ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣ ይረፍ ፡ ብለህ ፡ የጠራኸኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ እፎይ ፡ ብዬ ፡ ተደላድዬ ፡ ምኖርብህ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያለኝ ፡ ህብረት ማለት ፡ ለእኔ ፡ አለሜ ፡ ነው፥ አለሜ ነው ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ያገኘሁበት ምክንያቱ ፡ ነው ፡ የዘላለሜ ፡ የሰመረበት በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×) ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤