Loading
አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x) ዘንዶውን ፡ ገጥመህ ፡ ያሸነፍክ ፡ ጌታ በሃይል ፡ በስልጣን ፡ የምትበረታ ጽኑ ፡ ሃያላንን ፡ ሁሉ ፡ ያሸነፍክ የሃያል ፡ ሃያል ፡ ኢየሱስ ፡ ብርቱ ፡ ነህ አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በስልጣንህ ፡ ቃል ፍጥረት ፡ እስኪደነቅ ፡ ሰርተሃቸዋል ስላልተገኘልህ ፡ ከቶ ፡ ለአንተ ፡ አቻ ስምህ ፡ ገነነ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ሃይልህ ፡ ከሃያላን ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል ውሃን ፡ እንደግምብ ፡ ቀጥ ፡ አድርጐ ፡ ያቆማል ከአጥፊዎችም ፡ እጅ ፡ ክንድህ ፡ ያስጥላል የይሁዳ ፡ አምበሳ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ሃይልህን ፡ ሳያውቁ ፡ የተነሱብህ አስከትተው ፡ ጦር ፡ የዘመቱብህ ክንድህ ፡ ገጥሟቸው ፡ ተሸንፈዋል ስማቸው ፡ ጠፍቶ ፡ አንተ ፡ ነግሰሃል አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ሰማይ ፡ ምድርን ፡ በስልጣንህ ፡ ቃል ፍጥረት ፡ እስኪደነቅ ፡ ሰርተሃቸዋል ስላልተገኘልህ ፡ ከቶ ፡ ለአንተ ፡ አቻ ስምህ ፡ ገነነ ፡ እስከምድር ፡ ዳርቻ አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ያለህ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለህ ዙፋንህ ፡ ተነቃንቆ ፡ ተገርስሶ ፡ የታለ እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.