Loading
Singer
አዝ፦ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ አገር ፡ መርጬ ፡ ተናግሬአለሁ ፡ በማንነትህ ፡ ስለተመካሁ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ የሆነ ፡ አባት ፡ አለኝ ፡ ልዩ ፡ የምልበት ሆነህ ፡ አግኝቼሃለሁ ፡ ከእስትንፋሴ ፡ ቀርበህ ከምልህም ፡ በላይ ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) አዝ፦ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ (፪x) በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ ስሜ ፡ ተፅፎ ፡ በሕይወትህ ፡ መዝገብ ይህም ፡ ሳያንሰኝ ፡ በምድር ፡ ስታስብ መጽዓተኝ ፡ ሰው ፡ መሆኔን ፡ ሳውቀው የጌታዬ ፡ ጣት ፡ ጓዳዬን ፡ ሞላው በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የወደድኩት ፡ ጌታ በፍቅሩ ፡ ማረከኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ የመረጥኩት ፡ ጌታ የእራሱ ፡ አደረገኝ ፡ መጥቶ ፡ በዝግታ አዝ፦ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ፍቅርህ ፡ በዛ (፪x) በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ምህረትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ራቁቱን ፡ ቆሞ ፈውስ ፡ ይላል ፡ ቃል ፡ ገጣጥሞ ወግ ፡ ማዕረግ ፡ ረስቶ ፡ ፍፁም ፡ እርካታ በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ሰላም ፡ አፎይታ የተገረማችሁ ፡ በሚያስገርም ፡ ጌታ ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በደስታ (፪x) የተደነቃችሁ ፡ በሚያስደንቅ ፡ ጌታ ደስታችሁን ፡ ግለጹ ፡ በሆታ ፡ በዕልልታ (፪x) አዝ፦ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ (፪x) በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ በጐነትህ ፡ በዛ በዛ ፡ ለእኔስ ፡ በዛ ፡ ቸርነትህ ፡ በዛ ሃሌሉያ ፡ አሜን