Loading
Singer
Updated 3d ago
አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው የወደዳቸውን ፡ ፈጽሞ ፡ እስከመጨረሻው ፡ ወደደ ልጆቹን ፡ ከበደል ፡ ሊያነፃ ፡ በእራሱ ፡ ላይ ፡ ሞትን ፡ ፈረደ ከሞት ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ያየለ ፡ የበረታ ፡ ፍቅር ፡ ይዞት ኢየሱስ ፡ እራሱን ፡ ከፈለ ፡ የእኔ ፡ መጥፋት ፡ አሳዝኖት እነሆ ፡ ሲነጋና ፡ ሲመሽ ፡ ይህን/የእርሱን ፡ ፍቅር ፡ አስታውሰዋለሁ ሌለ ፡ ምሰጠው ፡ የለምና ፡ ተመስገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ እለዋለሁ (፪x) አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው ፍቅር ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ ታወቀ ፡ በስራው ፡ በኃይሉ ፡ በርትቶ ሰማይን ፡ ከምድር ፡ አስታረቀ ፡ በምህረቱ ፡ ጉልበት ፡ ጐትቶ የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ ፈረሰ ፡ ሆነ ፡ እርቅ ፡ ሰላም ፡ ደስታ የራቀው ፡ በሙሉ ፡ ቀረበ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዙፋን ፡ በጌታ አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ቸርነቱ ፡ አደራረጉ ፡ አስገርሞኛል በእውቀት ፡ በችሎታና ፡ ጥበቡ ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ ግዛት ፡ አድርሶኛል (፪x) እንዴት ፡ እንደሆነ ፡ ባላውቅም ፡ ኧረ ፡ ለምን ፡ ለምን ግን ፡ ይህንን ፡ ብቻ ፡ አውቃለሁ ፡ እኔ ፡ መወደዴን ይህንን ፡ ብቻ ፡ አውቃለሁ ፡ የወደደኝን በጉያው ፡ በእቅፉ ፡ አስገብቶ ፡ እንደሰወረኝ አውቃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እንደሚያስብልኝ (፪x) አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው