Loading
Singer
አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ ለተጨነቀ ፡ ልቡ ፡ እረፍት ፡ አግኝቶ ጉዞውን ፡ ቢጀምር ፡ ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር ፡ አቅንቶ ሰይጣን ፡ በተንኮል ፡ በወጥመዱ ፡ አጥሮ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋበት ጌታም ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ወጥመዱን ፡ ሰባብሮ ፡ በሩን ፡ ከፈተለት አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡ በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ መዋጋትን ፡ እንዲለምድ ፡ ሸለቆ ፡ ወርዶ ከቤት ፡ ከንብረቱ ፡ ከነፍሱ ፡ አብልጦ ፡ ጌታውን ፡ ወዶ ሰልፉ ፡ በረታና ፡ ክፉኛ ፡ ተጠቅቶ ፡ እጅና ፡ እግሩ ፡ ዝሎ ኢየሱስ ፡ ደርሶለት ፡ ድልን ፡ አወጀለት ፡ ባላንጣውን ፡ ጥሎ አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ እጆቹን ፡ በእርፉ ፡ ላይ ፡ አንዴ ፡ አሳርፏል ወደኋላ ፡ ማየት ፡ ነውር ፡ በመሆኑ ፡ ሥራውን ፡ ቀጥሏል እምነት ፡ ሳይጓደል ፡ አደራ ፡ ሳይበላሽ ፡ ተጠንቅቆ ፡ ታግሎ እፎይ ፡ ማለቱ ፡ ነው ፡ በክብር ፡ ተራራ ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ (፪x)