Loading
Singer
አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x) ደመናም ፡ ውኃም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆውን ፡ የሚሞላ በእርሱ እታመናለሁ ፡ በክንዶቹ ፡ ጥላ ጌታን ፡ ተስፋ ፡ አድርገው ፡ የሚጠባበቁ እንዳይጠፉ ፡ አውቃለሁ ፡ ከቶም ፡ እንዳይወድቁ አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x) ሰማያት ፡ ተናውጠው ፡ በክብሩ ፡ ይወርዳል የልጆቹ ፡ ነገር ፡ ጌታ ፡ ግድ ፡ ይለዋል ታምኜ ፡ እቆማለሁ ፡ በዓለቱ ፡ ላይ በፍጽሜው ፡ ዘመን ፡ ዐይኖቹን ፡ እስካይ አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x) የልጅነት ፡ ስልጣን ፡ እንዲያው ፡ ተሰጥቶኛል ስሙ ፡ በግንባሬ ፡ ማኅተም ፡ ሆኖኛል አምላክሽ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ አትበለኝ ፡ ጠላቴ አይቆይም ፡ ይመጣል ፡ ፈጥኖ ፡ ረዳቴ አዝ፦ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ የሚያስደንቀውን ፡ ምህረቱን በእኔ ፡ ላይ ፡ የገለጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስገን (፪x)