Loading
Singer
አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ የበረታ ፡ ሰልፍ ፡ ሲከበኝ ፡ ከኋላ ፡ ከፊት ቆይቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት እርሱም ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ሊያዳምጠኝ እንባዬን ፡ በእጁ ፡ ጠርጐ ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አፅናናኝ አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ ነፍስህ ፡ ብትራቆት ፡ ፍፁም ፡ ባዶ ፡ ስትሆን ያለህን ፡ አራግፈህ ፡ ተዘርፈህ ፡ ስታይ ፡ ራስህን ያሳለፍካቸውን ፡ ድሎች ፡ አስብ ፡ ተስፋህ ፡ ይለምልም ተንበርክከህ ፡ ብትቆይ ፡ ደግሞ ፡ መዳሰስህ ፡ አይቀርም አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ ከድካም ፡ የበረቱ ፡ ሰዎች ፡ በድል ፡ ያለፉ ከኢየሱስ ፡ በስተቀኝ ፡ በላይ ፡ የተሰለፉ መንግሥታትን ፡ ድል ፡ ነስተው ፡ ያንን ፡ ምሽግ ፡ የናዱ የፀሎት ፡ ሰዎች ፡ ናቸው ፡ ጠላት ፡ ያርበተበዱ አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ በትዕግሥት ፡ ፀጥታ ፡ በፀሎት ፡ ቆይታ መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ