Loading
Singer
በጥበብህ ፡ በችሎታህ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ፡ ጌታ (፪x) ዕውቀትህ ፡ የተለየ ፡ ፍጥረት ፡ እንዳንተ ፡ አልሰማ ፡ አላየ (፪x) (አሃሃ) ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብልህም (አሃሃ) ፡ ከዚያም ፡ ትልቃለህ (አሃሃ) ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር (አሃሃ) ፡ በማን ፡ ልመስልህ ከምልህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፬x) ሰው ፡ ከፍታ ፡ መጨረሻ ፡ መርገጫህ ፡ ነው ፡ ላንተ ፡ መነሻ (፪x) ታች ፡ ብወርድ ፡ ላይ ፡ ቢወጣ ፡ የሚመስልህ ፡ አንድም ፡ ታጣ ታች ፡ ብወርድ ፡ ላይ ፡ ቢወጣ ፡ የሚያህልህ ፡ አንድም ፡ ታጣ (አሃሃ) ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ ሆኜ (አሃሃ) ፡ ስምህን ፡ ባውድስ (አሃሃ) ፡ እንኳን ፡ ልጨርሰው (አሃሃ) ፡ ከመሃሉም ፡ እልደርስ ጥበብህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ዕውቀትህ ፡ ሠፊ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ገዢዎችን ፡ ትሾማለህ ፡ ሲያሻህ ፡ ደግሞ ፡ ታወርዳለህ ገዢዎችን ፡ ትሾማለህ ፡ ሲያሻህ ፡ ደግሞ ፡ ትሽራለህ ልዕልናህ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ካንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለ (፪x) (አሃሃ) ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ ሆኜ (አሃሃ) ፡ ስምህን ፡ ባውድስ (አሃሃ) ፡ እንኳን ፡ ልጨርሰው (አሃሃ) ፡ ከመሃሉም ፡ እልደርስ ከምልህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ልገልፅህ ፡ አልችልም ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x) ላምልክ ፡ እንደገና ፡ አሃ (፫x) አምላኬ ፡ ነህና ላንግሥ ፡ እንደገና ፡ አሃ (፫x) ንጉሤ ፡ ነህና (፪x)