Loading
Singer
በተዓምራትህ ፡ እየተገረምኩ በተዓምራትህ ፡ እየተደነቅኩ ዛሬም ፡ ላመልክህ/ላለነግስህ ፡ መቅደስህ ፡ ገባሁኝ (፪x) አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x) ሁልጊዜ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ስትሰራ ተነግሮ ፡ ተነግሮ ፡ አያልቅም ፡ ሥራህ ፡ ቢወራ (፪x) ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ ትሆናለህ ፡ ልዩ ተዓምር ፡ ስትሰራ ፡ ዓይኖቼ ፡ አንተን ፡ አዩ (፪x) በአንደኛው (፪x) ፡ ስገረም ፡ ሌላኛው ፡ ሲመጣ የአምላኬ ፡ የአድራጐቱ ፡ ብዛት ፡ ከውስጤ ፡ ሳይወጣ (፪x) የአሰራሩ ፡ ሚስጥር ፡ ለእራሴ ፡ ሳይገባኝ በኃያልነቱ ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ መራኝ (፪x) አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x) ከፈተው ፡ ከፈተው ፡ አፌንም ፡ እንዳመሰግነው አስችሎኝ ፡ እንዲሁ ፡ እንዳልቀመጥ ፡ ምክንያቴን ፡ አበዛው (፪x) ብዙ ፡ እያደረገ ፡ ዛሬ ፡ ላይ ፡ አቆመኝ በብቃቴ ፡ ሳይሆን ፡ በተዐምሩ ፡ አኖረኝ (፪x) አዝ፦ ይሄው ፡ የሽቶዬ ፡ መዓዛ ይሽተት ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላ ምክንያት ፡ አብዝቼ ፡ ላምልክ ፍቅርህ ፡ ወሰን ፡ የለው ፡ ልክ (፭x)