Loading
Singer
ለእኔ ፡ ቀኑ ፡ ጨልሞ ፡ መስማት ፡ እንጂ ፡ ማየት ፡ አልችል ጥዋት ፡ ልለምን ፡ የወጣሁ ፡ መሽቶ ፡ በሰው ፡ ነው ፡ ምገባው ትንሽ ፡ ትልቅ ፡ መሪዬ ፡ የሰው ፡ ፍቃድ ፡ ማደሪያዬ የእድሜዬን ፡ ግማሽ ፡ ቆጠርኩ ፡ ጨለማውን ፡ ለመድኩ መጣ ፡ ኢየሱስ ይሄ ፡ የአለም ፡ ብርሃን ዓይኖቼን ፡ ከፈተ ፡ በእውርነቴ ፡ ሃገር ታሪኬ ፡ ተለወጠ (፪x) የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ማረኝ ፡ ብዬ ፡ ተከፈተ ፡ ብርሃኔ መልካምነቱን ፡ አየሁት ፡ በዚህች ፡ በአጭሯ ፡ ዘመኔ ተጥዬ ፡ የነበርኩ ፡ ያምስኪኑ ፡ እኔ ፡ ነኝ መንገደኛ ፡ የማያየኝ ፡ አሳዛኝ ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ በሀጥያቱ ፡ ወደቀ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደቀቀ ብለው ፡ ሰዎች ፡ ፈርዱ ፡ ስብራቴን ፡ ሳይረዱ ደጉ ፡ ጌታ ፡ ከሰማይ ፡ አየኝ ከውድቀቴ ፡ አነሳኝ ፡ ቁስሌን ፡ ፈውሶ አከበረኝ ፡ መልሶ (፪x) በታምራት ፡ የሚያኖረኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያስብልኝ የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ባልጋዬ ፡ ላይ ፡ ተኝቼ ፡ ለአመታት ፡ ሸትቼ መልዐኩ ፡ ሲያናውጠው ፡ ማን ፡ ሊከተኝ ፡ ወደ ፡ ውሃው ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ የለኝ ፡ እኔ ፡ የምለው ፡ ሚረዳኝ ቀርቦ ፡ ችግሬን ፡ አየና ፡ ተራመድ ፡ ሂድ ፡ ተነሳና ያለው ፡ ጌታ ፡ ለካ ፡ ዘመዴ ፡ ነው ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ የሚሰማው ሽባነቴን ፡ ሽሮ ፡ አቆመኝ ፡ ቀይሮ ፡(፪x) በታምራት ፡ የሚያኖረኝ ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያስብልኝ የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ