Loading
Singer
አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም (፪x) ውድቀቴን ፡ ሲጠብቅ ፡ አሁንም ፡ ያ ፡ ክፉ አታልፊውም ፡ ሲለኝ ፡ ቀኖቹም ፡ ሲከፉ የነፍሴ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰና እኔን ፡ አሻገረኝ ፡ ታሪክ ፡ ለወጠና አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም (፪x) ጠላት ፡ ሲያስለቅሰኝ ፡ ሸለቆ ፡ እያሳየ እግዚአብሔር ፡ ከሠማይ ፡ ሰምቶ ፡ ዘንበል ፡ አለ እንባዬን ፡ አብሶ ፡ ደስታን ፡ አለበሰኝ ለልቤ ፡ መጽናናት ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ሆነልኝ አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም (፪x) ገበናዬን ፡ ሸፊኝ ፡ ሚስጥር ፡ ተካፋዬ ጉድለቴን ፡ ሞላልኝ ፡ በእርሱ ፡ በጌታዬ በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በመንፈስ ፡ ባርኮኛል የመንግሥቱ ፡ ወራሽ ፡ ርስቱ ፡ አድርጐኛል አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም (፪x) ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አይቶ ፡ የሚራራ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለምና ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ላብዛለት ፡ ምሥጋና ክብር ፡ ያገኘሁት ፡ በአምላኬ ፡ ነውና አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም በእግዚአብሔር ፡ በሥሙ ፡ ታምኜ ፡ አላፈርኩም ሥሙንም ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላጣሁም ከመልካም ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ አልጐደልኩም (፪x)