Loading
Singer
አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x) ሙታን ፡ ሳለን ፡ ያኔ ፡ በደል ፡ የተሞላን ስንወጋው ፡ ቁስልህን ፡ ኃጥያት ፡ እየሰራን ፍቅርህ ፡ በርትቶ ፡ ነው ፡ ቁጣህን ፡ የሻረው ልበ ፡ ቅን ፡ ሆነህ ፡ ነው ፡ ክፉውን ፡ የማርከው (፪x) አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x) ተሰበረ ፡ ቀንበር ፡ ሸክም ፡ ተራገፈ ከእንግዲህ ፡ እስር ፡ የለም ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ አለፈ ከድካም ፡ በረታን ፡ ጉልበት ፡ አግኝተናል ኃይልን ፡ በምትሰጠን ፡ ባለ ፡ ድል ፡ ሆነናል (፪x) አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x) ከተጠመደብን ፡ ወጥመድ ፡ አስመለጥከን መኖሪያ ፡ ከለላ ፡ መሸሸጊያ ፡ ሆንከን ነጣቂም ፡ አይነካን ፡ ምን ፡ ድፍረት ፡ አግኝቶ ይኸው ፡ ምህረትህን ፡ አይቶ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ በዝቶ (፪x) አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፪x) ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ትከሻ ፡ ስንቱን ፡ አዝሎ ፡ አኑሯል የአባትነት ፡ ምክርህ ፡ ጠማማን ፡ አቅንቷል ምን ፡ ያልሆንከው ፡ አለ ፡ ለመረጥከን ፡ ለእኛ ጉያህ ፡ መግባት ፡ ቻልን ፡ ሆነን ፡ እድለኛ (፪x) አዝ፦ በሰማይ ፡ እንዳሉ ፡ ከዋክብቶች እንደማይቆጠሩ ፡ አሸዋዎች እንደዚያው ፡ ምህረትህ ፡ በዝታልናለች ይኸው ፡ እስከ ፡ ዛሬ አኑራናለች ፡ ገና ፡ ታኖረናለች ፡ አሃ (፬x)