Loading
Singer
አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x) ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x) ቀድሞ ፡ እንደምኖረው ፡ የሞት ፡ ኑሮ ፡ አልኖርም ኃጢአት ፡ ለመቃረም ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ አልወርድም ጥፋት ፡ አያምረኝም ፡ መንፈሱ ፡ ገዝቶኛል ቅዱስ ፡ ደሙን ፡ ረጭቶብኝ ፡ ቅዱስ ፡ አድርጐኛል አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x) ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x) ሁሉን ፡ እርግፍ ፡ አድርጌ ፡ ጠቀመኝ ፡ መምጣቴ ውዴ ፡ አላሳፈረኝም ፡ ሆነኝ ፡ እረዳቴ አሁን ፡ አያይም ፡ ዓይኔ ፡ ወደ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ የሰው ፡ እጅ ፡ አላይም ፡ አግኝቻለሁ ፡ አጉራሽ አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x) ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x) ጩኸቴን ፡ ይሰማል ፡ ድምጼ ፡ ይናፍቀዋል አሸናፊው ፡ አምላኬ ፡ ድል ፡ አስለምዶኛል እምበረከካለሁ ፡ ዛሬም ፡ በጸጋው ፡ ዙፋን ፡ ስር ሲቀበር ፡ አያለሁ ፡ የተጋባኝ ፡ ችግር አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x) ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፪x) የገዛኝ ፡ ተገዛልኝ ፡ አዛዡ ፡ ሆኛለሁ ባለማዕረግ ፡ ሆንኩኝ ፡ ስልጣን ፡ አግኝቻለሁ የመድሃኒቴን ፡ ስም ፡ ስጠራ ፡ መደንገጥ ልማድ ፡ አድርጐታል ፡ ዲያቢሎስ ፡ መፈርጠጥ አዝ:- በእርሱ ፡ ተለወጥኩኝ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ (፪x) ውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ፈካሁ ፡ እንደ ፡ አበባ ባለውለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፫x) ባለዉለታዬ ፡ ይባረክ ፡ ጌታዬ (፫x)