Loading
Singer
ብርሃን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ብርሃን ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው ጨለማን ፡ ያበራል ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ ነው በጨለማ ፡ ላለ ፡ ብርሃን ፡ ነው ለተጨነቀ ፡ ሕዝብ ፡ መጽናናት ፡ ነው ከሃጥያት ፡ የሚያድን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እውነትና ፡ መንገድ ፡ ሕይወትም ፡ ነው ለተጠማ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ይሰጣል በእርሱ ፡ የሚታመን ፡ መች ፡ ይራባል ዘላለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ይኖራል ባባቱ ፡ ቤት ፡ መሰማሪያ ፡ ያገኛል በእርሱ ፡ የሚያምኑ ፡ ይድናሉ ከሃጥያት ፡ በደሙ ፡ ይነጻሉ የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ አብረው ፡ ይከብራሉ ኢየሱስ ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ይገኛል የሚፈልገው ፡ ልብ ፡ ደስ ፡ ይሰኛል ሸክምን ፡ ያራግፋል ፡ እረፍት ፡ ያሰጣል አእምሮና ፡ ልብን ፡ ያስርፋል