Loading
Singer
በስጋም ፡ በነፍስም ፡ የባረከኝ (፪x) ደጋግሞ ፡ የባረከኝ በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ የባረከኝ (፪x) ደጋግሞ ፡ የባረከኝ ጌታ ፡ አልበቃህም ፡ ወይ ፡ ባርከኽኝ (፪x) እኔ ፡ እንኳን ፡ ብል ፡ በቃኝ አንተ ፡ መቼ ፡ እረካህ ፡ ባርከኽኝ (፪x) እኔ ፡ እንኳን ፡ ብል ፡ እፎይ ሀዘን ፡ የሌለበት ፡ በረከት ፡ ደስታ ፡ ብቻ ፡ የሆነ እየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ ባርከህኛል ፡ በል ፡ ሂድ ፡ ልጄ ፡ ብለህ ሀዘን ፡ የሌለበት ፡ በረከት ፡ ደስታ ፡ ብቻ ፡ የሆነ ኢየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ ባርከህኛል ፡ ተከናወን ፡ ብለህ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው አንዴ ፡ የሚወጣ ፡ ተመልሶ ፡ ደግሞ ፡ አንዴ ፡ የሚወርድ አይደል ፡ በረከቴ ፡ በምድር ፡ እንዳለው ፡ የሚመጣ ፡ የሚሄድ እየሱስን ፡ ሰጥተህ ፡ አንዴ ፡ ዘላለሜን ፡ አባ ፡ ባርከኽዋል እጠቀመዋለው ፡ መንዝሬ ፡ መንዝሬ እንኳን ፡ ለእኔ ፡ ለአለም ፡ ሁሉ ፡ ይበቃል በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በመንፈሳዊ ፡ ሁሉ ፡ በረከት ፡ ባረከኝ በልጁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሥምም ፡ ስላመንኩኝ ፡ ሁሉን ፡ አወረሰኝ የእርሱን ፡ በጐነት ፡ የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ ለዓለም ፡ አወራለው በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ የጐደለኝ ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ስላገኘው የኔማ ፡ የኔማ ፡ በረከት ፡ ሰላም ፡ የሞላበት ፡ ደስታ ፡ የሞላበት እየሱስ ፡ ያለበት የእኔማ ፡ የእኔማ ፡ በረከት ፡ የተትረፈረፈ ፡ ፈጽሞ ፡ የማያልቅ እየሱስ ፡ ያለበት ኢየሱስ ፡ ያለበት (፯x) ሰላም ፡ የሞላበት ኢየሱስ ፡ ያለበት (፯x) ኢየሱስ ፡ ያለበት በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በረከቴ ፡ እራሱ ፡ ነው ፡ በረከቴ ፡ ማንነቱ ፡ ነው