Loading
Singer
በእረኝነቱ ፡ ተመርቻለሁ ጠንቀቅ ፡ አድርጌም ፡ ድምፁን ፡ አውቃለሁ በአረንጓዴው ፡ መስክ ፡ ባማረው ፡ ላይ አንሰራፍቶኛል ፡ ሳይኖር ፡ ከልካይ አልፈራም ፡ አውሬ ፡ ደፋር ፡ አርጎኛል የአራዊት ፡ ድምፅ ፡ መቼ ፡ ያስፈራኛል ባለመናወጥ ፡ ከምንጩ ፡ ልርካ ከጭንቀት ፡ ማረፍ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ አሃ እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ (፬x) ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል ይህን ፡ የቅርብ ፡ ወዳጄን ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል ይህን ፡ የበረሃ ፡ ጓዴን ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል ይህን ፡ ሚስጢረኛዬን ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተለዪው ፡ ይሉኛል ይህን ፡ መልካም ፡ እረኛዬን አልለየውም ፡ አልለየውም ያለ ፡ እርሱ ፡ መኖር ፡ እኔስ ፡ አልችልም አልለየውም ፡ አልለየውም ያለ ፡ እርሱ ፡ ውበት ፡ ወዝም ፡ የለኝም (፪x) ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያልኩትን ፡ ያለ ፡ ከፍታዬ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያረገኝ ወገን ፡ ያልሆንኩትን ፡ በልጁ ፡ ልጅ ፡ አርጎ ፡ ማዕረግን ፡ ያሳየኝ የተደረገውን ፡ በጎነት ፡ ቸርነት ፡ አልችልም ፡ መሸከም የምልህ ፡ የለኝም ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመን ፡ ከፊት ፡ ፊቴ ፡ ቅደም ብርታቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ብርታቴ ህይወቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ህይወቴ ጉልበቴ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጉልበቴ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ መድኃኒቴ (፪x) መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x)