Loading
Singer
(ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው ፡ ልባርከ ፡ እየሱሴን ፡ ልባርከው) (፪x) በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ ባረክኝ የረገጥኩትን ፡ አወረሰኝ (ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጠው ፡ ለጌታ እስኪ ፡ ከፍ ፡ አርጉልኝ ፡ በልልታ) (፪x) የነገረኝን ፡ በሙሉ ፡ እስከሚያደርግልኝ ፡ ታምኖ የክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ የሆነው ሲጠማኝ ፡ ምንጭ ፡ አፈለቀ ፡ ሲርበኝ ፡ ደግሞ ፡ አጐረሰኝ ሰው ፡ ዓይንህ ፡ ላፈር ፡ ሲለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አንዴ ፡ ሳይሸሸኝ እንደበደሌ ፡ አልከፈለኝ ፡ ምህረቱ ፡ ስለእኔ ፡ በዝቷል በነፍስና ፡ በሥጋየ ፡ በረከቱ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቷል እንዴት ፡ ታዲያ ፡ ዝም ፡ ልበል ፡ ይህንን ፡ ሁሉ ፡ አይቸ ልስገድ ፡ ልውደቅ ፡ በግንባሬ ፡ ማደሪያው ፡ ቤቱ ፡ ገብቸ አዝ ልባርከ ፡ ጌታዬን በደሌ ፡ በፊቱ ፡ በዝቶ ፡ ያለቀ ፡ የሞትኩ ፡ ሲመስለኝ የጠላቴ ፡ ማስፈራራት ፡ ጩኸቱ ፡ ሲያርበደብደኝ በዘመርኩበት ፡ አንደበት ፡ ሙሾ ፡ለመውረድ፡ ስዳዳ የሞትን ፡ ወሬ ፡ ሰምቸ ፡ ለነፍሴ ፡ ሞትን ፡ ላረዳ ስዋከብ ፡ ከዚህ ፡ ወደዚያ ፡ ጭንቀቴን ፡ አይቶ ፡ ደረሰ የተዋጋኝን ፡ ተዋጋው ፡ እቅዱን ፡ አፈራረሰ ዛሬማ ፡ በኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ ሰው ፡ ያደረገኝን ፡ አምላኬን ፡ በዜማ ፡ እባርካለሁ አዝ ልባርከው ፡ ጌታዬን በሰማያዊ ፡ በረከት ፡ በመንፈስ ፡ ባርኮ ፡ ባረከኝ የምድሩንም ፡ አላጣሁም ፡ ይልቁን ፡ አትረፈረፈኝ ሳይሰለች ፡ የተሸከመኝ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ ቤቴን ፡ ባረከው ዓለም ፡ የነፈገችኝን ፡ ኢየሱስ ፡ እጥፍ ፡ አረገው ኢየሱስን ፡ ብሎ ፡ ወዝ ፡ አጣ ፡ ያሉኝ ፡ዛሬ ፡ አፈሩ ጌታ ፡ ሞገሴ ፡ መሆኑን ፡ በአፋቸው ፡ መሰከሩ ወጥመድ ፡ ቢዘጋጂልኝም ፡ ኢየሱስ ፡ እየቀደመ ሕይወቴን ፡ በረከት ፡ ሞላው ፡ ደረቅ ፡ በትር ፡ ለመለመ አዝ ልባርከው ፡ ጌታዬን እናንተም ፡ እንደኔው ፡ ጌታ ፡ በቀን ፡ በቀን ፡ የባረካችሁ በተሰደዳችሁበት ፡ ምድር ፡ እጅግ ፡ ያበዛችሁ የገዛችሁን ፡ ኢየሱስ ፡ ከግራችሁ ፡ ያስገዛላችሁ ጂራት ፡ ሳይሆን ፡ እንደቃሉ ፡ የሁሉ ፡ ራስ ፡ ያረጋችሁ እስኪ ፡ እናንተው ፡ ንገሩኝ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምን ፡ ይከፈላል ወደር ፡ ለሌለው ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ ምላሽ ፡ምንስ ፡ ይሰጣል ከአድማስ ፡ እስከ ፡ አድማስ ፡ ሙገሳ ፡ክብር ፡ ሙገሳ ፡ ይድረሰው ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ በአንደበቱ ፡ ይቀድሰው አዝ ልባርከው ፡ ጌታዬን