Loading
Singer
በጣም ፡ የከበረ ፡ እጅግ ፡ ያየለ ከወርቅ ፡ እንቁ ፡ ይልቅ ፡ የተሻለ በፍፁም ፡ ድርድር ፡ አብ ፡ የማያውቅበትን አንድያ ፡ ልጁን/ክንዱን ፡ ሰጠ ፡ ኢየሱስን አዝ፦ በቂ ፡ ነው ፡ ከበቂም ፡ በላይ (፫x) ለሰማይ ፡ ቢሉ ፡ ለምድሩም ፡ ሲሳይ ስቀበለው ፡ ያኔ ፡ እንደግል ፡ አዳኝ መዘገበው ፡ ስሜን ፡ በላይኛው ፡ ሰማይ የቅዱሳን ፡ ተስፋ ፡ በረከቴ ፡ ሆኖኛል ፡ ቀረኝ ፡ የምለው ፡ የለም ፡ አብ ፡ ጨርሶ ፡ ባርኮኛል ስቀበለው ፡ ያኔ ፡ እንደግል ፡ አዳኝ መዘገበው ፡ ስሜን ፡ በላይኛው ፡ ሰማይ የቅዱሳን ፡ ተስፋ ፡ ስጦታዬ ፡ ሆኖኛል ቀረኝ ፡ የምለው ፡ የለም ፡ አብ ፡ ሁሉንም ፡ ሰጥቶኛል ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባርኮት ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታስ ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ሰላም ፡ ምናለ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ አለም ፡ የሌላትን ፡ አገኘሁ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ ዓሣ ፡ በምድር/በየብስ ፡ ላይ ፡ ሕይወት ፡ አያምረው ከባህር ፡ እርቆ ፡ መኖር ፡ አያሰኘው ሁልግዜ ፡ መገኛው ፡ አንድ ፡ እና ፡ አንድ ፡ ነው ከውሀ ፡ የወጣ ፡ እለት ፡ መሞቻው ፡ ቅርብ ፡ ነው የእኔም ፡ ያለኢየሱስ ፡ ልክ ፡ እንዲህ ፡ ባዶ ፡ ነው ከመገኛ ፡ እርቆ ፡ መኖር ፡ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ከንቱ ፡ ነው የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ጠግቤ ፡ የሕይወት ፡ ውሀ ፡ ረክቼ ከእርሱ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ መገኛዬ ፡ አንድ ፡ እና ፡ አንድ ፡ ነው በረከቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ፦ በቂ ፡ ነው ፡ ከበቂም ፡ በላይ (፫x) ለሰማይ ፡ ቢሉ ፡ ለምድሩም ፡ ሲሳይ