Loading
Singer
ስለት ፡ ነበረብኝ ፡ ለኢየሱስ ፡ ለጌታ እንዲህ ፡ ካረገልኝ ፡ እስራቴን ፡ ከፈታ እንደመልካም ፡ አባት ፡ አንጀቱ ፡ ራርቶ አይዞህ ፡ ልጄ ፡ አለኝ ፡ ሳልጮህ ፡ ገና ፡ ሰምቶ (፪x) ሃጥያት ፡ እየሰራሁ ፡ እንዲያ ፡ እያደከምኩት የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩን ፡ እየዘነጋሁት ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ ግን ፡ ይከታተሉኛል አባብለው ፡ አምጥተው ፡ ቤቱ ፡ ያገቡኛል ፊቱ ፡ ያቆሙኛል አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ ከአቻምና ፡ አምና ፡ ከአምና ፡ ዘንድሮ የጌታ ፡ ውለታ ፡ አያልቅም ፡ ተቆጥሮ የምህረቱ ፡ ብዛት ፡ የፍቅር ፡ ጥልቀቱ ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገባ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ የጌታ ፡ ምህረቱ የፍቅር ፡ ዓይኖቹን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ያቀና በምክር ፡ እግሮቹን ፡ ወደኔ ፡ ያቀና እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ባርኮኛልና ይኸው ፡ መስዋእቴ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ከልቤ ፡ ምሥጋና አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ የሚያስጨንቀኝን ፡ ከሳሼን ፡ አዋርዶ ሳልመርጠው ፡ የመረጠኝ ፡ ሳልወደው ፡ እጅግ ፡ ወዶ ከአባቱ ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ የሚያዘጋጅልኝ ባለውለታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ይክበርልኝ ጌታ ፡ ይክበርልኝ ከአጥናፍ ፡ እስከ ፡ አጥናፍ ፡ ጌታን ፡ አክብሩክኝ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ በሉ ፡ ዘምሩልኝ የጌታ ፡ ውለታ ፡ መግለጫ ፡ ያላችሁ እስኪ ፡ እናምልከው ፡ ዕልል ፡ እያላችሁ ክበር ፡ እያላችሁ አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ (፪x) እስኪ ፡ ቆም ፡ ብላችሁ ፡ አስቡ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ እናንተን ፡ ለማዳን ፡ ስለሞተው ፡ ጌታ በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ የተንጠለጠለው ከዘላለም ፡ ጥፋት ፡ አንተን ፡ ለማዳን ፡ ነው አንቺን/እኛን ፡ ለማዳን ፡ ነው (፪x) አዝ፦ በቀራንዮ ፡ ያደረገልኝ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ ከቅዱሳን ፡ ጋር ፡ እሰግዳለሁ በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አዜማለሁ (፬x)