Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ ቅጠሌን ፡ አይተው ፡ የተመሰጡ ፍሬን ፡ ፍለጋ ፡ ቤቴ ፡ ስመጡ በጣፋጭ ፡ ዜማ ፡ እየጠራሁኣቸው ያለ ፡ ዉሃ ፡ እንዳሸኛቸው ፡ ። አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ ስምህ ፡ ተጠርተው ፡ ድንቅን ፡ ስሰራ የኔ ፡ ገድል ፡ እንዳይወራ መድረኩም ፡ እንኳ ፡ ብነቃነቅ አንተን ፡ አክብሬ ፡ ራሴን ፡ ልናቅ። አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ የውርንጫዋ ፡ የስራ ፡ ድርሻ ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ መድረሻ ጨርቅ ፡ ብነጠፍ ፡ ሆሳዕና ፡ ብባል ክብር ፡ ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ይገባል። አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ ባመጽ ፡ ተወልደን ፡ በኃጢኣት ፡ አድጋናል በጎውን ፡ ነገር ፡ ማን ፡ ያሳየናል በሚለው ፡ ትውልድ ፡ መካከል ፡ ስገኝ እውነትን ፡ ገላጭ ፡ ብርሃን ፡ አድርገኝ። አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በየቀኑ ፡ መጨረሻ ለትውልድ ፡ መፈወሻ ፡ አድርገኝ አንተን ፡ በመፍራት ፡ አሳድገኝ