Loading
ተስፋ ፡ ርቆ ፡ ሲዞር ፡ የሚደግፍ ፡ ጠፍቶ ዘንበል ፡ የሚል ፡ ማነው ፡ እንደጌታ ፡ ራርቶ ጊዜ ፡ ወቅቱን ፡ አይተው ፡ ሰዎች ፡ ሲቀየሩ ጌታ ፡ ግን ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ወረት ፡ የለው ፡ ፍቅሩ (፪x) መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ የሚተጋ ፡ የሚተጋ አላየሁኝም ፡ በቃሉ ፡ የሚገኝ ፡ የሚገኝ አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ብቻውን ፡ ታማኝ (፪x) ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x) ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ምኞቴ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ አንተን ፡ መታመኔ ፡ እኔ ፡ መች ፡ ከንቱ ፡ ነበረ (፪x) እሰዪ ፡ የልቤ ፡ ደረሰ ምርኮዬ ፡ በእርሱ ፡ ተመለሰ ተሞላ ፡ ልቤ ፡ በደስታ ልዘርም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x) እንግዲህ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ጨለማዬ ፡ በራ ከሸለቆ ፡ ወጣሁ ፡ ቆምኩኝ ፡ በተራራ (፪x) ጌታዬ ፡ ባንተ ፡ ምኞቴ ፡ ያሰብኩት ፡ ተሳካ አንተን ፡ መታመኔ ፡ እኔ ፡ ልክ ፡ ነበር ፡ ለካ (፪x) ልክ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ልክ ፡ ነው እንዳለው ፡ ነው ፡ ለኔ ፡ ያደረገው ሁኔታ ፡ ቃሉን ፡ አለወጠው በእውነትም ፡ ጌታዬ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፪x) መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ፡ እስኪነጋ ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ የሚተጋ ፡ የሚተጋ አላየሁኝም ፡ በቃሉ ፡ የሚገኝ ፡ የሚገኝ አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ብቻውን ፡ ታማኝ ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ ታማኝ ፡ ነዉ ፡ ታማኝ (፪x) በሀሩሩ ፡ ጥላ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ ምስኪን ፡ የምታግዝ ፡ ፀሎት ፡ የምትሰማ በሀሩሩ ፡ ጥላ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ እኔን ፡ የምታግዝ ፡ ፀሎት ፡ የምትሰማ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.