Loading
Singer
አንተን ፡ እየሰጋሁ ፡ እኔን ፡ ያመንኩበት እየጠረጠርኩህ ፡ በእኔ ፡ እርግጥ ፡ የሆንኩበት ለካ ፡ የከንቱነት ፡ የሞኝነት ፡ ዘመን ፡ ነው ዛሬ ፡ ግን ፡ ነቅቼ ፡ እምነቴ ፡ ነህ ፡ እላለሁ ለካ ፡ የከንቱነት ፡ የሞኝነት ፡ ዘመን ፡ ነው ዛሬ ፡ ግን ፡ ሲገባኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ/ማኅተሜ ፡ እላለሁ (፪x) አንተ ፡ እምነቴ ፡ ነህ (፭x) ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ አንተ ፡ ተስፋዬ ፡ ነህ (፪x) አንተ ፡ ማህተሜ ፡ ነህ (፪x) አንተ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ እምነቴ ፡ ነህ ባለማወቅ ፡ ጠንቅ ፡ በልበ ፡ ደንዳናነት ፡ የጨለምኩ ይህን ፡ ዓለም ፡ ለሚገዛ ፡ ለክፉ ፡ መንፈሥ ፡ ባሪያ ፡ ነበርኩ በዘላለም ፡ ቁጣ ፡ ተጥዬ ፡ ከአብ ፡ ሕይወት ፡ የራቅኩኝ ገና ፡ ከፍጥረቴ ፡ ሙት ፡ ነበርኩኝ የማመጣው ፡ የዋኖስ ፡ ደም ፡ አይደለም ፡ ያነፃኝ አብን ፡ እንዳየው ፡ ጸጋህ ፡ ነው ፡ የረዳኝ የማመጣው ፡ የበግ ፡ ደም ፡ አይደለም ፡ ያነፃኝ አብን ፡ እንዳምነው ፡ ጸጋህ ፡ ነው ፡ የረዳኝ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአቅምህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ጸጋህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ስራህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ትጋትህ በደሌን ፡ ተሸክመህ ፡ ለዓለም ፡ እና ፡ ለአብ ፡ አንዴ ፡ ታይተሀል ፅድቅን ፡ አልብሰህ ፡ ለዘላለም ፡ በቀኙ ፡ አኑረሀል መልከጼዴቄ ፡ ባንተ ፡ እኔ ፡ ዳንኩኝ ከአቤል ፡ ደም ፡ ባየለ ፡ በደምህ ፡ ነፃሁኝ ከከንቱ ፡ እሩጫ ፡ ባንተ ፡ ታቅቤ ሞት ፡ ላይከጅለኝ ፡ መንደር ፡ ቀይሬ በምሕረትህ ፡ ብርታት ፡ ከጠላት ፡ ኮበለልኩ ከድካሜ ፡ ይልቅ ፡ ሃይልህንም ፡ አመንኩ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ፀጋህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በሥራህ በቃ ፡ ዳንኩኝ ፡ በአንተ ፡ አቅም ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ስራህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ ፀጋህ ለእኔ ፡ መዳኛ ፡ ነው ፡ መሞትህ