Loading
Singer
አዝ፦ ሆኖልኛል ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x) ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (፪x) መገረም ፡ ሞልቶኛል ፡ ጌታ ፡ መውደዱ ፡ ገኖ ፡ ሲወጣ ቆሜ ፡ ከመዘመር ፡ በቀር ፡ ምለውን ፡ አንዳች ፡ እስካጣ የክብሩ ፡ ጸዳል ፡ ሲያበራ ፡ እኔን ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሲጣራ ከልካይ ፡ አልነበረም ፡ ፊቱ ፡ ሲበራ ፡ ለእኔ ፡ መብራቱ አዝ፦ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x) ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ (እለዋለሁ) የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (በዓይኔ) (፪x) ዓይነጋም ፡ ብሎ ፡ ንጋቴን ፡ ሲረግምብኝ ፡ ሰማሁና እኔም ፡ ጠላት ፡ ያለውን ፡ ለአምላኬ ፡ ተናገርኩና ቀን ፡ አለው ፡ አምላኬ ፡ ከላይ ፡ በዓይኖቹ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲያይ ጠላት ፡ መግቢያውን ፡ አጣ ፡ ዓይኔ ፡ አያየው ፡ ተቀጣ አዝ፦ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ሆኖልኛል ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፊቴ ፡ ወጥቶልኛል (፪x) ነጋ ፡ ጠባ ፡ ተመስገን ፡ እለዋለሁ (እለዋለሁ) የሞት ፡ ደጃፍ ፡ ተዘግቶ ፡ አይቻለሁ (በዓይኔ) (፪x) በቃ ፡ ብሎ ፡ ገስጾ ፡ ወጀቡን ፡ ለእኔ ፡ አዞ አሳለፈኝ ፡ ጌታዬ ፡ ላክብረው ፡ በዜማዬ (፪x) ላክብረው ፡ በዜማዬ (፬x) ፤ ላክብረው ፡ በተራዬ (፬x)