Loading
Singer
አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x) ሰላሳ ፡ ስምንት ፡ አመት በአልጋዬ ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ ተኝቼ (ኦሆ ፡ ኦሆ) መልዓኩ ፡ ሲያናውጠው ወደ ፡ ውሃው ፡ ሚከተኝ ፡ አጥቼ (ኦሆ ፡ ኦሆ) አቅም ፡ የለኝ ፡ ወገን ፡ የለኝ ውስጤ ፡ እያለ ፡ ተማረረ (ኦሆ ፡ ኦሆ) እምባ ፡ ቀደሙት ፡ ዓይኖቼ ልቤም ፡ እጅጉን ፡ አዘነ አበቃልኝ ፡ በቃ ፡ ዛሬ ሊቀጥል ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ህመሜ ብዬ ፡ ሳስብ ፡ በትካዜ ጌታ ፡ ቆሟል ፡ ከአጠገቤ (፪x) አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x) ጨለማ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ኑሮ ብርሃን ፡ አጥቶ ፡ ዓይኔ ፡ ታውሮ (ኦሆ ፡ ኦሆ) ወጣሁ ፡ ምጽዋትን ፡ ጥየቃ እንደድሮ ፡ እንደወትሮ (ኦሆ ፡ ኦሆ) ምንድነው ፡ ኢሄ ፡ ጩኸቱ ብዬ ፡ ጠየኩ ፡ የሚያልፍ ፡ ሰው (ኦሆ ፡ ኦሆ) ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ መጥቶ ፡ ነው ፈዋሹ ፡ እያለፈ ፡ ነው የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ማረኝ ፡ ብዬ አላለፍከኝ ፡ አባብዬ ፊትህንም ፡ አዞርክልኝ ጨለማዬን ፡ ገፈፍክልኝ (፪x) አዝ፦ በቃ ፡ የሰቆቃው ፡ ኑሮ ለየለት ፡ ደረሰ ፡ ዘንድሮ በሰላም ፡ ሂድ ፡ አለኝ ሕይወቴን ፡ ቀይሮ (፪x) ምንድነው ፡ እርሱ ፡ በዛብኝ ችግርና ፡ መከራዬ (ኦሆ ፡ ኦሆ) የሞት ፡ ጥላ ፡ አጠላብኝ አታየኝም ፡ ወይ ፡ ጌታዬ (ኦሆ ፡ ኦሆ) ከአባቶቼ ፡ እንደተማርኩት ከቃልህ ፡ እንዳነበብኩት (ኦሆ ፡ ኦሆ) ጩኸት ፡ ሰምተህ ፡ መልሰሃል ለስንቱ ፡ ሕይወት ፡ ሆነሃል የእኔስ ፡ ቀን ፡ መቼ ፡ ነው ፡ አልኩኝ ተንበርክኬ ፡ ተማጸንኩኝ ጸሎቴም ፡ ተሰማልኝ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በቃህ ፡ አለኝ (፪x) በቃ ፡ በቃ ፡ በቃ በቃ ፡ በቃ ፡ በቃ የሰቆቃው ፡ ዘመን ከእኔ ፡ ላይ ፡ አበቃ (፬x)