Loading
Singer
አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ መጥተናል ፡ ተቀበለን በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) የቤትህን ፡ ተድላን ፡ ሰላም ፡ ተቀምተን ከፍ ፡ ካድረከን ፡ ከጉያህ ፡ ውስጥ ፡ ወተን ጠላትህ ፡ ረጋግጦ ፡ ብዙ ፡ አጐሳቁሎናል በምህረትህ ፡ ጐብኘን ፡ ፊትህ ፡ ይሻለናል የዓለምን ፡ ምርኩዝ ፡ ኀጢአት ፡ ተደግፈን በስራ ፡ ሳንለይ ፡ እንዲሁን ፡ በአፋችን አሁን ፡ ምኑ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ሕይወታችን በጌታ ፡ ቤት ፡ ሆነን ፡ እየተገፋፋን አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ መጥተናል ፡ ተቀበለን በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) ይብቃን ፡ አሁን ፡ ይብቃን ፡ እንደሬት ፡ ይምረረን ኀጢአትን ፡ እንጥላው ፡ በንሰሃ ፡ ታጥበን እንደጌታ ፡ ያለ ፡ የትም ፡ አናገኝም አይተነው ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ቆሻሻውን ፡ ዓለም በስም ፡ ክርስትና ፡ ብለን ፡ ተሸፍነን በቃላት ፡ ታጅበን ፡ ለሚያየን ፡ ሰው ፡ መስለን ምንም ፡ አልተለወጥን ፡ ገባ ፡ ብሎ ፡ ለአየን ሌላ ፡ ስም ፡ የለንም ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ታሪካችን አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ መጥተናል ፡ ተቀበለን በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) "እንደ ፡ ምህረትህ ፡ ብዛት እንደቸርነትህ ፡ መጠን ለአምጻችንና ፡ ለኀጢአታችን ፡ ፍሬ አሳልፈህ ፡ አትስጠን" ዘር ፡ ቀለምን ፡ ለየን ፡ የእኛ ፡ ጉድ ፡ አያልቅም አንድ ፡ ያደረከንን ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ዐይናችን ፡ ጨልሞ ፡ ከፋፍለን ፡ ብናይም ባሪያ ፡ ጨዋ ፡ ብሎ ፡ ቃሉ ፡ አይለያየንም ክርስቶሥን ፡ ለብሶ ፡ አይሁድ ፡ ግሪክ ፡ የለም የጸና ፡ ቃል ፡ አለን ፡ ማንም ፡ አይሽረውም እንመለስ ፡ አሁን ፡ ጌታ ፡ መሃሪ ፡ ነው እርሱ ፡ ይቅር ፡ ሊለን ፡ ሁሌም ፡ ዝግጁ ፡ ነው አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ መጥተናል ፡ ተቀበለን በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x) አጣፍጠን ፡ ብንዘምር ፡ አንደበትን ፡ ስለን ጌታ ፡ ሚፈልገው ፡ መቀደሳችንን ድምጹን ፡ እናዳምጠው ፡ እስኪ ፡ እንተላለፍ በስራ ፡ እንለይ ፡ በቃል ፡ ከመለፍለፍ የድፍረት ፡ ኀጢአት ፡ አናፍርም ፡ ስንሰራ እንደ ፡ ኤሊ ፡ ልጆች ፡ በነውር ፡ ስንኮራ ምክር ፡ ግሳጼንም ፡ እንሰማም ፡ ብለናል በመስዋዕቱ ፡ ሥጋ ፡ ልባችን ፡ ደንድኗል አዝ፦ በንሰሃ ፡ ለመመለስ ወደ ፡ ዙፋንህ ፡ ለመድረስ መጥተናል ፡ ተቀበለን በደላችንን ፡ ይቅር ፡ በለን (፪x)