Loading
Singer
አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x) የእምነት ፡ አባቶቼን ፡ ሳስባቸው ፡ በደም ፡ የደመቀ ፡ ታሪካቸው በወህኒ ፡ በስራት ፡ በመከራ ፡ በጉድጓድ ፡ በዋሻ ፡ በተራራ የተቅበዘበዙ ፡ እሳት ፡ የበላቸው ፡ ለቃልኪዳን ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ ለእንጀራቸው ምሳሌነታቸው ፡ እንድከተል ፡ አርገኝ ፡ በልክስክስ ፡ ቦታ ፡ ከመሞት ፡ ጠብቀኝ አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x) ሰው ፡ ሁሉ ፡ ቢክድህ ፡ እኔ ፡ አልክድህ ፡ ካንተ ፡ ይልቅ ፡ እራሴን ፡ አልወድ ብዬ ፡ ስመጻደቅ ፡ ስቀናጣ ፡ ያቺ ፡ ፈታኝ ፡ ሰዐት ፡ ስትመጣ ኢየሱስን ፡ አላውቅም ፡ ብዬ ፡ እንዳልራገም ፡ አፌን ፡ ጠብቅልኝ ፡ ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ነገ መስቀሌን ፡ አግዘኝ ፡ ብለህ ፡ ስትለምነኝ ፡ የዓለምን ፡ እሳት ፡ ከመሞቅ ፡ አድነኝ አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ በሞቱ ፡ እንድመስለው : እመኛለሁ (8x) የአንድ ፡ ሰሞን ፡ ወሬ ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ ፡ መስቀል ፡ ያልፈተነው ፡ ጉብዝና የአንድ ፡ ሰሞን ፡ ሙቀት ፡ ሀሌሉያ ፡ ፡ አይሆንም ፡ መለኪያ ፡ መታወቂያ ካላለፍኩኝ ፡ በቀር ፡ ያቺን ፡ ቀውጢ ፡ ሰዓት ፡ አንተን ፡ አስከብሬ ፡ በመከራ ፡ እሳት ፍጻሜዬ ፡ እንዲያምር ፡ ጉዞ ፡ እንዲሰምርልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ፈሪ ፡ ነኝ ፡ እምነት ፡ ጨምርልኝ አዝ፦ ወደ ፡ ሙታን ፡ ትንሳኤ ፡ ለመድረስ ፡ ቢሆንልኝ በሞቱ ፡ እንድመስለው እመኛለሁ (8x) ደካማው ፡ ስጋዬ ፡ ሲስገበገብ ፡ የዓለም ፡ ነገር ፡ እንደው ፡ አይጠገብ አንዱን ፡ ስይዝ ፡ ሌላው ፡ እንዳያምረኝ ፡ ኑሮዬ ፡ በቃኝ ፡ ማለትን ፡ አስተምረኝ ስለ ፡ ስምህ ፡ ክብር ፡ ለመንግስትህ ፡ መስፋት ፡ ሁሉን ፡ መስዋአት ፡ ላድርግ ፡ ለሚጠፉ ፡ ነፍሳት ገንዘቤ ፡ ገንዘብህ ፡ ቤቴም ፡ የአንተ ፡ ቤት ፡ እንድሞት ፡ አድርገኝ ፡ የጻድቃንን ፡ ሞት