Loading
Singer
እውነቱ ፡ አዳነኝ ፡ እውነት ፡ ነው ፈልጐ ፡ አገኘኝ ፡ ፍቅር ፡ ነው አደራረጉ ፡ ልዩ ፡ ነው ከምንገምተው ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ ልናገር ፡ ተደርጐልኛል ቀንበሬም ፡ በርሱ ፡ ተሰብሮልኛል አርነት ፡ ወጣሁ ፡ ነፃ ፡ አውጥቶኛል ከዚያች ፡ ሩጫ ፡ እኔን ፡ ፈቶኛል የተፈታ ፡ ሰው ፡ የተለቀቀ መውጣት ፡ መግባቱ ፡ የተጠበቀ ያመሰግናል ፡ ያመሰግናል ፡ ጊዜው ፡ ሁኔታ ፡ መች ፡ ያስቆመዋል ያመሰግናል ፡ ያመሰግናል ፡ ማግኘት ፡ ማጣቱ ፡ መች ፡ ያስቆመዋል ያኔ ፡ በልጅነት ፡ ገና ፡ መጀመሪያ ጌታ ፡ ተናገረኝ ፡ በኔ ፡ እንደሚሰራ የተናገረው ፡ ቃል ፡ ጊዜውን ፡ ጠብቆ ሲፈጸም ፡ በዓይኔ ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ አይረሳም ፡ እኮ (፪x) አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት እንደማይረሳ ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት እንደማይጥል ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት ረዳት ፡ መሆኑን ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት አንድ ፡ የገባኝ ፡ ነገር ፡ የተረዳሁት ትልቅነቱን ፡ ነው ፡ በዘመኔ ፡ ያየሁት ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ረዳት ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ አባት ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ፈዋሽ ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ፍቅር ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ልዩ ፡ ነው ፣ ብለው ፡ አይበቃኝ ፡ ልዩ ነው እርሱ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነው እርሱ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነው እርሱ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው እርሱ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x)