Loading
Singer
አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን የሕይወት ፡ ምርጫችን እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x) ከሁሉ ፡ የሚበልጠውን ፡ ተመልክተው ከየምድሩ ፡ ጉድጓድ ፡ ተቅበዝብዘው ነፍስን ፡ ከሚዋጋ ፡ ምኞት ፡ ርቀው ወንዙን ፡ ተሻገሩ ፡ አሸንፈው (፫x) አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን የሕይወት ፡ ምርጫችን እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x) ቅን ፡ ከምትመስል ፡ ሰፊ ፡ መንገድ ወጥተን ፡ በጠባቡ ፡ ስንሰደድ በዚህ ፡ ጐዳና ፡ ላይ ፡ ሕይወት ፡ አለ ቆርጦ ፡ ለሚከተል ፡ የታደለ (፫x) አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን የሕይወት ፡ ምርጫችን እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x) ባለ ፡ ፀጋ ፡ ሲሆን ፡ ደህይቶልን ባለ ፡ ማዕረግ ፡ ሲሆን ፡ ተዋርዶልን እውነተኛውን ፡ ፍቅር ፡ ገለጸልን እኛም ፡ በእርሱ ፡ መንገድ ፡ እንሄዳለን (፫x) አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን የሕይወት ፡ ምርጫችን እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x)