Loading
Singer
አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x) ቅዱሳን ፡ መላዕክት ፡ ሱራፌል ፡ በሠማይ ፡ ያሉ ሳያቋርጡ ፡ ዘወትር ፡ ለአንተ ፡ ይሰግዳሉ ፀሐይ ፡ ጨረቃ ፡ ከዋክብት ፡ ቁጥር ፡ የሌላቸው በቀን ፡ በማታ ፡ እንዲያበሩ ፡ የፈጠርካቸው የጥበብህ ፡ ስራ ፡ ምሳሌ ፡ ናቸው አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x) ደማናዎችህ ፡ እንደጥጥ ፡ የተባዘቱ ማሰሮው ፡ ሲያዘነብል ፡ በልጉ ፡ ክረምቱ የሠማይ ፡ አዕዋፍ ፡ በየዘር ፡ በየወገኑ ማን ፡ ይናገራል ፡ የዕውቀትህ ፡ ልኩ ፡ መጠኑ በየቋንቋቸው ፡ ሲያመሰግኑህ አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x) የምድር ፡ ፍጥረታት ፡ ሕያዋን ፡ ተንቀሳቃሾች ሰዎች ፡ እንስሳት ፡ አራዊት ፡ የባሕር ፡ አሶች ውቅያኖስ ፡ ወንዙ ፡ ሸለቆው ፡ ደኑ ፡ ተራራ አቤት ፡ ሲያስደንቅ ፡ የቃልህ ፡ የእጅህ ፡ ስራ ሁሉም ፡ በቋንቋው ፡ ክብርህን ፡ ያውራ አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x) በዓለም ፡ ታሪክ ፡ በዘመን ፡ በአመታት ፡ መሃል የሌለህበት ፡ ያለአንተስ ፡ የሆነ ፡ የታል ነገሥታት ፡ ሲያልፉ ፡ ኃያላን ፡ ወድቀው ፡ ሲቀሩ ድንቅ ፡ የተባሉ ፡ ግኝቶች ፡ ሲያልፉ ፡ ሲሻሩ የእኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በክብሩ አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፪x) አቤቱ ፡ ስራህ ፡ አሳብህ ፡ ሁሉም ፡ ድንቅ ፡ ነው ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሚይስደንቅ ፡ መዳናችን ፡ ነው በመጀመሪያ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የነበረው ፡ ቃል በድንግል ፡ ማህጸን ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ መድን ፡ ተወልዷል ጨካኙን ፡ ዘንዱ ፡ በመስቀል ፡ ራሱን ፡ ቀጥቅጦ አመተ ፡ ፍዳን ፡ በአመተ ፡ ምህረት ፡ ለውጦ ሁሉን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ በቀኝህ ፡ ለተቀመጠው በክብር ፡ በሥልጣን ፡ ዳግመኛ ፡ ለሚገለጠው ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ይኸው አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሁሉ ፡ ላይ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ስምህ ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ (፫x) ይባረክ ፡ ይባረክ ፤ ይባረክ ፡ ይባረክ