Loading
Singer
በመጀመሪያ ፡ በመጀመሪያ (፫x) እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x) ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x) ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ይመጣል የልቤ ፡ መሻት ፡ ይሆናል እንደተጻፈው ፡ አደርጋለሁ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ሰው ፡ ባለው ፡ በሃብቱ ፡ ምን ፡ ቢኮራ ቢማር ፡ ሊቅ ፡ ቢሆን ፡ ታሪክ ፡ ቢሰራ ጌታ ፡ ከሌለው ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ነው በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x) ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፪x) ዳዊትም ፡ ኖረ ፡ እድሜ ፡ ዘመኑን መጀመሪያ ፡ አርጐ ፡ እግዚአብሔርን የሚቋቋመው ፡ አልነበረም መንግስቱ ፡ ጸና ፡ ለመለመ የእግዚአብሔር ፡ ልቡ ፡ እንዳረፈበት እንደልቤ ፡ እንዳለው ፡ እንደኮራበት እንደእምነት ፡ አባቴ ፡ እንደዳዊት አስደስታለሁ ፡ የጌታን ፡ ልብ አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፫x) ሌላው ፡ ተከታይ ፡ ነው (፬x)