Loading
Singer
የሳተ ፡ ይመለስ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ከግድፈቱ የወደቀስ ፡ ይጠገን ፡ የለም ፡ ወይ ፡ ከስብራቱ አይኖቹን ፡ ሲያቀና ፡ በተስፋ ፡ ወደአንተ ሲማፀን ፡ ምህረትን ፡ እየወተወተ አይችልም ፡ መጨከን ፡ አንጀትህ ፡ የአባትነትህ አጥበህ ፡ ታነፃለህ አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ይሄንን ፡ ላውራልህ አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ (፪x) በጨለማ ፡ ብቀመጥ ፡ ብርሀኔ ፡ ነህ የሀጢያት ፡ ሸክም ፡ ቢያጐብጠኝም ፡ ታቀናኛለህ ተስፋዬ ፡ ይቅርታ ፡ መጽናኛዬም ፡ ፊትህ ፡ ነው ስለቸርነትህ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ምኖረው ሲሰማኝ ፡ መኖርህ ፡ ሳስተውል ፡ መገኘትህን መንፈሴ ፡ ያንስራራል ነቅቶ ፡ ያዳምጥሀል ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ይልሃል አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ (፪x) ጉስቁልናዬን ፡ ስታይ ፡ አዘንክልኝ እራርተህ ፡ እጅህን ፡ ዘረጋህ ፡ አቅፍህ ፡ ልታነሳኝ ግድ ፡ የሚልህ ፡ ለኔ ፡ መጥፋቴን ፡ ማትወደው ፊትህ ፡ ለኔ ፡ በራ ፡ በደሌንም ፡ ተውከው እንደባሪያ ፡ መሆን ፡ ሳያንሰኝ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ልጅ ፡ አልከኝ እራሴን ፡ ልስጥህ ፡ ዝቅ ፡ ልበልልህ ላንተው ፡ ኖሬ ፡ ላንተው ፡ ልሙትልህ አዝ፦ ብደክም ፡ ወድቄ ፡ እንዳልቀር ፡ ፀጋህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያግዘኛል ምህረትህ ፡ ከቁጣ ፡ ይፈጥናል ፡ እንድኖር ፡ ምክንያት ፡ ሆኖኛል አልመካም ፡ መች ፡ ቆሜ ፡ ባቅሜ ባትረዳኝ ፡ ሆነህ ፡ አጠገቤ ፡ ከጐኔ (፪x) በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤትህ ፡ እገባለሁ (፪x) ስለምህረትህ ፡ ጌታ ፡ አመልክሃለሁ (፪x) በፊትህ ፡ ሞገስ ፡ ያገኘሁት አይደለም ፡ በእራሴ ፡ ያቆሙኩት የፅድቅ ፡ የሥራ ፡ መልካም ፡ ነገር ምህረትህ ፡ ድፍረት ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው የፀጋህ ፡ ማስቻሉ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ስምህን ፡ ላክብረው (፪x)