Loading
Singer
አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1] የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x) ራሳቸውንና ፡ ገንዘብን ፡ የሚወዱ ተድላን ፡ የሚፈልጉ ፡ እውነትን ፡ የሚክዱ በቃኝን ፡ የማያውቁ ፡ የማያመሰግኑ ይሆናሉ ፡ ተብሏል ፡ ሳያዩ ፡ የማያምኑ ዘመኑ ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ ያስፈራል ኧረ ፡ ክርስቲያን ፡ ሆይ ፡ ብትነቃ ፡ ይሻላል (፪x) አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1] የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x) ለጊዜያዊ ፡ ስልጣን ፡ ሌላውን ፡ የሚያሳድዱ መልካምን ፡ የሚጠሉ ፡ ክፋትን ፡ የሚወዱ ለወሬ ፡ የሚሮጡ ፡ ለሀሜት ፡ የሚቸኩሉ የቀድሞውን ፡ ፍቅር ፡ ከውስጣቸው ፡ የጣሉ በመንደርህ ፡ አሉ ፡ ለራስህ ፡ ጠንቀቅ ፡ በል ዘመኑን ፡ ዋጅ ፡ እንጂ ፡ አጉል ፡ አጉል ፡ ቦታ ፡ አትዋል (፪x) አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1] የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x) ፍቅር ፡ የሌላቸው ፡ እርቅን ፡ የማይሰሙ ለጥቅማቸው ፡ ሲሉ ፡ ፍትሕ ፡ የሚያጣምሙ ምህረት ፡ የማያደርጉ ፡ ድሃን ፡ የሚበድሉ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ በአፍ ፡ የሚደልሉ ያለ ፡ ሥርዓት ፡ ጥሰው ፡ የሚሄዱትን ፡ ሁሉ ዝም ፡ አትበል ፡ ገስጽ ፡ ይህን ፡ ይላል ፡ ቃሉ (፪x) አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1] የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x) እኔ ፡ ከተመቸኝ ፡ ምን ፡ ቸገረኝ ፡ ባዮች በቃሉ ፡ የማይኖሩ ፡ ሰነፍ ፡ ክርስቲያኖች በዚህ ፡ ዓለም ፡ ንዋይ ፡ የሚደለሉ ፡ ሞኞች ለሚያምኑ ፡ እንቅፋት ፡ የሚሆኑ ፡ ዝንጉዎች አሉ ፡ በየአገሩ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ሰው ፡ ሆይ ፡ ሽሽ እልፍ ፡ በልና ፡ ይህን ፡ ዘመን ፡ ፈትሽ ተላላ ፡ አትሁን ፡ ክርስቲያን ፡ ሆይ ፡ ንቃ ከወጽመድ ፡ ልታመልጥ ፡ አንሳ ፡ የጦር ፡ ዕቃ አዝ፦ ነገር ፡ ግን ፡ በመጨረሻው ፡ ቀን ይመጣል ፡ የሚያስጨንቅ ፡ ዘመን [1] የተባለው ፡ ጊዜው ፡ ይህ ፡ ነው ይሻልሃል ፡ ወንድሜ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ አስበው (፪x)