Loading
Singer
በለቅሶ ፡ የዘራሁትን ፡ በደስታ ፡ አጨድኩት ምርኮዬም ፡ ተመልሷል ፡ በብዙ ፡ በረከት ሚስጢሩ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ የማምለጫው ፡ መንገድ እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ግሩም ፡ ነህ ፡ ማለት ጌታን ፡ ላመስግን ፡ ባልሆነው ፡ በሆነው በዚያ ፡ ሠፈር ፡ ብቻ ፡ ድልን ፡ ተቀዳጀሁ ዛሬ ፡ እንደ ፡ ትላንት ፡ መች ፡ አለቅሳለሁ ቁልፉን ፡ አስይዘኸኝ ፡ የምሥጋናን ፡ በትር ጠላቴን ፡ ረግጬ ፡ አንበረክከዋለሁ በፎከረብኝ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ እፎክራለሁ ከሚውጠው ፡ ጉድጓድ ፡ ከሚያሰጥም ፡ ማጥ አውጥቶ ፡ አቆመኝ ፡ እግሮቼን ፡ በዓለት መች ፡ ተንሸራተትኩኝ ፡ በቃሉ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ድልን ፡ ተቀዳጀሁ ፡ እንዲያውም ፡ በአምላኬ ልግለጥ ፡ ልግለጥ ፡ ምርጡን ፡ የጦር ፡ መሳሪያዬን ላንበልብለው ፡ ዛሬ ፡ ጠላቴም ፡ ይሸበር የመንፈስን ፡ ሠይፍ ፡ አጥብቄ ፡ ይዣለሁ ጠላቴን ፡ ቆርጬ ፡ አጋድመዋለሁ ከደም ፡ ከሥጋ ፡ ጋር ፡ ውጊያን ፡ አቁሜያለሁ ነገሩ ፡ ገብቶኛል ፡ አሁን ፡ ነቅቻለሁ ዘመን ፡ መጣ ፡ መጣ ፡ የዜማ ፡ ወራት ከሁሉም ፡ ይሰብሰብ ፡ ይግባ ፡ ለአምላክ ከንፈሮቼን ፡ ልክፈት ፡ አንደበቴም ፡ ያውራው ቅኔም ፡ ይደርደር ፡ ከዝማሬ ፡ ጋራ ታማኝነትህን ፡ ማዳንህን ፡ ልንገር ሌላ ፡ ሰው ፡ አልሻም ፡ እኔው ፡ ነኝ ፡ ምስክር ቀረ ፡ መሸማቀቅ ፡ አቀርቅሮ ፡ መሄድ ቀንበር ፡ ተሰበረ ፡ ቀንቅ ፡ ብዬ ፡ እንድሄድ