Loading
Singer
እኔም ፡ እንዲህ ፡ እንዲህ ፡ ወግ ፡ ደረሰኝ ከመቅበዝበዝ ፡ እሱ ፡ በቃ ፡ ሲለኝ ያ ፡ መራራ ፡ ሕይወቴ ፡ ጣፈጠ በኢየሱሴ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ አይዞህ ፡ ባየለኝ ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባይረዳኝ ማንስ ፡ ሊጎበኘኝ ፡ ማንስ ፡ ሊቀርበኝ በቃ ፡ ሲል ፡ አበቃ ፡ ያ ፡ ዘመን ፡ አለፈ ጭጋጉ ፡ ከፊቴ ፡ ይኸው ፡ ተገፈፈ ለእኔስ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ አድርጎልኛል ያደላል ፡ ብላችሁ ፡ ማን ፡ ይቀየመኛል ከናት ፡ ካባት ፡ በላይ ፡ ስለተመቸኝ እንደሱ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሁሌ ፡ እላላሁኝ አዝ፦ ያ ፡ መራራ ፡ ቀን ፡ ያለፈው ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x) ጭጋጉ ፡ የተገፈፈው ፡ በሱ ፡ ነው (፪x) ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ልበለው (፪x) በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት ይነገራል ፡ የእርሱ ፡ ደግነት እኔስ ፡ ገና ፡ ገና ፡ በልጅነት አይቻለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ምህረት ሲርበኝም ፡ ከእጁ ፡ በልቻለሁ ያንን ፡ ሁሉ ፡ መች ፡ እዘነጋለሁ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ (፪x) አይቼዋለሁ ፡ የሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x) እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x) አዝ፦ ያ ፡ መራራ ፡ ቀን ፡ ያለፈው ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x) ጭጋጉ ፡ የተገፈፈው ፡ በሱ ፡ ነው (፪x) ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ልበለው (፪x) በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት ይነገራል ፡ የእርሱ ፡ ደግነት