Loading
Singer
ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በክብር ፡ ላለኸው ለሞትና ፡ ለሲዖል ፡ ኃይልህን ፡ ያስታወቅከው የዘላለም ፡ ደጆች ፡ ላንተ ፡ ይከፈቱ የጽድቅ ፡ ንጉሥ ፡ ግባ ፡ ዛሬም ፡ እንደ ፡ ጥንቱ አዝ:- በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የምትቀመጥ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታይ በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የምትቀመጥ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ና እንደተስፋ ፡ ቃልህ ፡ መጣህ ፡ ወደ ፡ ምድር ለገባው ፡ ሚስጥሩ ፡ ታየ ፡ የአንተ ፡ ክብር የማይሻር ፡ የጸና ፡ የትንቢት ፡ ቃል ፡ ይዘን እስክትመጣ ፡ ኢየሱስ ፡ እንጠብቅሃለን አዝ:- በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የምትቀመጥ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታይ በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ የምትቀመጥ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ና ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) ፡ ሃሌሉያ ፡ (ሃሌሉያ) በምሥጋና ፡ (በምሥጋና) ፡ እናንግሠው ፡ (እናንግሠው) አዝ:- በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ (በኪሩቤል ፡ ላይ) ፡ የምትቀመጥ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታይ በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ (በኪሩቤል ፡ ላይ) ፡ የምትቀመጥ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ና (፬x)