Loading
Singer
የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ለልጆቹ ይህ ፡ ነው ፡ መንገዱ ፡ ለምርጦቹ ብድራታቸውን ፡ ያስተዋሉ የጌታን ፡ መስቀል ፡ ይመርጣሉ አዝ፦ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ ለዚች ፡ ዓለም ፡ የሚመቹ ነውረኛውን ፡ ትርፍ ፡ ያከማቹ በኩርነታቸውን ፡ አቃለዋል በሥጋ ፡ ምቾት ፡ ተጠምደዋል አዝ፦ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ ጌታን ፡ አክብሮ ፡ መጐስቆሉ እንደ ፡ ጉድፍ ፡ የትም ፡ መጣሉ የመዳን ፡ ምልክት ፡ ክብራችን ድል ፡ መምቻችን ፡ ነው ፡ መስቀላችን አዝ፦ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ ጌታን ፡ ምሰሉ ፡ በኑሮአችሁ ከጠፊ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ አላችሁ ውጡ ፡ ተለዩ ፡ እባካችሁ ፍፁማን ፡ ሁኑ ፡ በልባችሁ አዝ፦ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ፡ ሊኖሩ ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ይሰደዳሉ እንደ ፡ ወርቅም ፡ ይፈተናሉ በመጨረሻም ፡ ሁሉንም ፡ አልፈው የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳሉ