Loading
Singer
ቃል አለኝ የሚፈፀም አምላኬ የነገረኝ/3 ህልም አለኝ የሚፈታ ጌታዬ ያሳየኝ/3 በጅምር አይቀርም የኔ ነገር ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2 እገሰግሳለሁ ወዳየልኝ ክብር ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 ዮርዳኖስ ቢሞላም አይቀርም መሻገር ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 ዘልቄ ሄዳለው በምድሪቱ ስፋት ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 በጅምር አይቀርም የኔ ነገር ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2 ይጨምራል ገና የቅባቱ ጉልበት ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 አልቆምም ሄዳለው ጌታ ብሏልና ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 አይሆንም አልልም ሆኖ ስለማየው ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ/2 በጅምር አይቀርም የኔ ነገር ሳይጨርስ አያርፍም እግዚአብሔር/2 አምላኬ ሲጠራኝ ከዛ መንደር ለትልቅ ቁም ነገር/3 እየሱስ ሲያመጣኝ ከዚያ ሰፈር ለትልቅ ቁም ነገር/3 ለሚያልፈው ለዚ አለም ነገር ጨከን በል ልቤ አትሸበር/2 ለምን ተበሳጨ ያ ጠላቴ አይቶ መቀባቴን/3 ስለምን ተመኘው ጠላት ሞቴን አይቶ መቀባቴን/3 ከዚህም የበለጠ ገና አለኝ አምላኬ እግዚአብሔር ያሰበልኝ/2