Loading
Singer
ተወራረድኩበት ፡ በዚህ ፡ ታማኝ ፡ ጌታ አይጥለኝም ፡ አልኩኝ ፡ እኔንም ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ፡ (ኦሆ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ) የድሮ ፡ ቃልኪዳን ፡ በልቤ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ፎከርኩኝ ፡ በአምላኬ ፡ አይተወኝም ፡ ከቶ ፡ (ኦሆ ፡ እኔን ፡ ከቶ) እንደ ፡ ዓይኑ ፡ እኔን ፡ ሲያይ ገረመኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ምህረቱ ፡ ገንኖ ፡ ነው ፡ ለካ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ጨለማ (፪x) ዞር ፡ ዞር ፡ አልኩና ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ (ወደ ፡ ግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ) ከፊትም ፡ ከኋላም ፡ ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ ፡ (ሲጠፋ ፡ የሚረዳኝ) ዓይኖቼን ፡ ሳነሳ ፡ ወደ ፡ የዋሁ ፡ ጌታ ፡ (ወደ ፡ ጀግናው ፡ ጌታ) ችግሬን ፡ አጣሁት ፡ እሱን ፡ ባየሁ ፡ ለታ ፡ (እሱን ፡ ባየሁ ፡ ለታ) ጌታ ፡ እንደሌለው ፡ እንደሌለው እንደማንም ፡ እኔስ ፡ አይደለሁም ቀና ፡ ስል ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ወደ ፡ አምላኬ ልመናዬን ፡ ሰማኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) በቅጡ ፡ አውቀዋለሁ ፡ የኔን ፡ ጌታ ያሻግራል ፡ ቃሉማ ፡ መልካም ፡ ቦታ ሰንቆም ፡ ላከልኝ ፡ መልሴን ፡ ፈጥኖ ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በቃ ፡ ብሎ (፪x) ምንድነው ፡ ሚሰማው ፡ በከተማው ፡ ወሬ ሞቷል ፡ አትበሉ ፡ በሕይወት ፡ አለሁ ፡ ዛሬ (ኦሆ ፡ አለሁ ፡ ዛሬ) እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ሃሳብ ፡ ወደ ፡ ግብጽ ፡ ቢወርድም ህልሙ ፡ ሳይፈጸም ፡ ባለራዕይ ፡ አይሞትም (በፍጹም ፡ አይሞትም) እንደ ፡ ዓይኑ ፡ እኔን ፡ ሲያይ ገረመኝ ፡ ጌታ ፡ ከላይ ምህረቱ ፡ ገንኖ ፡ ነው ፡ ለካ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ጨለማ (፪x)