Loading
Singer
በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x) አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x) ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x) እጅ ፡ ጭነህ ፡ መርቀኸኛል ፡ ተባረክ ፡ ብለህ ለጠላቴ ፡ መልስን ፡ ሰጠኸው ፡ አትንካው ፡ ብለህ እልፍ ፡ ስል ፡ የበረከት ፡ ምንጭ ፡ ያጋጥመኛል ገና ፡ ሳልደርስ ፡ ስራዬን ፡ ሰርተህ ፡ ጠብቀኸኛል ጠብቀኸኛል (፬x) አቤት ፡ ያንተስ ፡ ነገር ፡ ስንቱ ፡ ይነገር አቤት ፡ ያንተስ ፡ ስራ ፡ ስንቱ ፡ ይወራ (፪x) በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x) አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x) ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x) ስላለፈው ፡ ልቤ ፡ ሲነሳ ፡ ሊያመሰግንህ በመንገዴ ፡ ፈጥረህ ፡ ጠበቅከኝ ፡ ሌላ ፡ ተዓምር ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እጁን ፡ ባፉ ፡ ላይ ፡ እስኪጭን ፡ ድረስ በሩቅ ፡ በቅርብ ፡ ተዓምር ፡ ተባለ ፡ ሆነኸኝ ፡ ሞገስ ሆነኸኝ ፡ ሞገስ (፬x) አቤት ፡ ያንተስ ፡ ነገር ፡ ስንቱ ፡ ይነገር አቤት ፡ ያንተስ ፡ ስራ ፡ ስንቱ ፡ ይወራ (፪x) በሕይወቴ ፡ ዘመን (፰x) አልተውከኝም ፡ ፈጽሞ ፡ አልረሳኸኝም (፪x) ለአንድ ፡ አፍታ ፡ አልረሳኸኝም (፪x)