Loading
Singer
አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት (፪x) ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለም ለመዳኔ ፡ ምክኒያት ፡ ምንም ፡ አልፈጠርኩ ታሪኬ ፡ እንዲያምር ፡ ከክብሩ ፡ ወረደ ሕይወቱን ፡ ሊሰጠን ፡ እራሱን ፡ አዋረደ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x) አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት ሰራሁት ፡ የምለው ፡ አከናወንኩት ዛሬ ፡ ለመድረሴ ፡ እኔስ ፡ ለፋሁበት የምለው ፡ የለኝ ፡ ድካሜ ፡ ነው ፡ ቀላ ግን ፡ በእርሱ ፡ ምህረት ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x) አዝ፦ በኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ ሰው ፡ አይበረታ ፡ በኃይሉ አቅሜ ፡ እንዳልል ፡ የለኝም ፡ ጉልበት እኔን ፡ ለማዳን ፡ ነው ፡ ስቃዩ ፡ የበዛው የደም ፡ ላብ ፡ ያላበው ፡ በመስቀል ፡ የሞተው ሞቴን ፡ የሞተልኝ ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል የዘለዓለም ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ አድርጐኛል ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፬x)