Loading
Singer
አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ይኖራል (፪x) ከትከሻው ፡ መሃል ፡ ተማምኖ ፡ ያድራል (፪x) ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ) ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ) እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ) ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ) አምላኬ ፡ መታመኛዬ ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ የፀና ፡ ግንብ ፡ ነውና ፡ በሥሙ ፡ እጓደዳለሁ ገና ፡ ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ ከማያልቀው ፡ ቸርነቱ በዘይት ፡ ሊያለመልመኝ ፡ ተክሎኛል ፡ እና ፡ በቤቱ እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፪x) አዝ፦ በእግዚአብሔር ፡ የተወደደ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ይኖራል (፪x) ከትከሻው ፡ መሃል ፡ ተማምኖ ፡ ያድራል (፪x) ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ) ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ) እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ) ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ) የሕይወትን ፡ ምንጭ ፡ አግኝቼ ፡ ከተድላው ፡ ፈሳሽ ፡ ጠጥቼ ዳግመኛ ፡ እኔ ፡ አልጠማም ፡ ረቻለሁ ፡ ለዘለዓለም በብርሃኑ ፡ ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጨለማውም ፡ ተሸነፈ ተማምኜ ፡ እኖራለሁ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ስላረፈ እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፬x) ለሚታመኑበት ፡ መታመኛ (ኦሆ ፡ መታመኛ) ነውና ፡ የሚያኮራ ፡ መልካም ፡ እረኛ (ኦሆ ፡ መልካም ፡ እረኛ) እኔም ፡ ከጥላው ፡ በታች ፡ ተጠልያለሁ (ኦሆ ፡ ተጠልያለሁ) ፅኑ ፡ ክንዱን ፡ ተደግፌ ፡ አመልከዋለሁ (ኦሆ ፡ አመልከዋለሁ) እርሱን ፡ ተማምኜው ፡ እኖራለሁ በክንፉቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አርፌያለሁ (፬x)