Loading
Singer
አዝ፦ ለምን ፡ እሩቅ ፡ ልሂድ ፡ ለምን ፡ ጐረቤቴ ፍቅርህን ፡ ካየሁት ፡ አለሁበት ፡ እኔ የፍቅርህ ፡ ምሳሌ ፡ የመውደድህ ፡ ምሳሌ አለሁኝ ፡ እኔ የማክበርህ ፡ ምሳሌ ፡ የማንሳትህ ፡ ምሳሌ አለሁኝ ፡ እኔ (፪x) ምህረትህን ፡ አልከለከልከኝም በጠላት ፡ እጅ ፡ አልዘጋህብኝም ሆነህልኝ ፡ የመጠጊያ ፡ ቤቴ እረሳሁት ፡ ሃዘኔን ፡ ምሬቴን ተከተለኝ ፡ ቸርነት ፡ ምህረትህ ጨመረልኝ ፡ የሕይወት ፡ ውበት በፍቅርህ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ ነገር አዝ፦ ለምን ፡ እሩቅ ፡ ልሂድ ፡ ለምን ፡ ጐረቤቴ ፍቅርህን ፡ ካየሁት ፡ አለሁበት ፡ እኔ የፍቅርህ ፡ ምሳሌ ፡ የመውደድህ ፡ ምሳሌ አለሁኝ ፡ እኔ የማክበርህ ፡ ምሳሌ ፡ የማንሳትህ ፡ ምሳሌ አለሁኝ ፡ እኔ ባትመግበኝ ፡ እጅህ ፡ ምህረትህ እጠፋለሁ ፡ ከዓይንህ ፡ በቅፅበት የምህረትህ ፡ ጥገኛ ፡ ናት ፡ ነፍሴ ታስፈልገኛለህ ፡ እንደ ፡ እስትንፋሴ አዘነብከው ፡ ፍቅርህን ፡ በላዬ አረሰረሰኝ ፡ ዘልቆ ፡ በጓዳዬ አያልቅብህ ፡ አንተስ ፡ ደግነት የትልቅ ፡ የትንሹ ፡ አባት ይነበብ ፡ ይነበብ ፡ ታሪኬ ይነገር ፡ በእኔው ፡ አፍ (፪x) በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ተወልጄ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ታድጌያለሁ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ሮጬ ፡ ሮጬ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ እሄዳለሁ (፫x) በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ተወልጄ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ታድጌያለሁ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ ሮጬ ፡ ሮጬ በእግዚአብሔር ፡ ምህረት ፡ እሄዳለሁ