Loading
Singer
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ በአንድ ፡ አባት ፡ ልጆች ፡ ላይ የተገፋፋ ፡ ሰው ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ያመልክሃል አንድ ፡ ላይ ፡ ያመልካል ውስጡን ፡ እያመመው ፡ ጥላቻው ፡ በርትቶ ወድሃለው ፡ ይላል ፡ ህዝብህ ፡ ቤትህ ፡ ገብቶ አንድ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ስንበላም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንጠጣም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንገባም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንወጣም ፡ አንድ ፡ ላይ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ዘምን ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ኖረናል ውስጥ ፡ ውስጡን ፡ ተባልተን ፡ ግን ፡ ተለያይተናል ምን ፡ ያደርጋል ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን የስስት ፡ ጨርቃችን ፡ መጨረሻው ፡ ብል፡ ነው ለዛሬ ፡ ያልሆነ ፡ ፍቅራችን ፡ ለመች ፡ ነው ኧረ ፡ ለማንስ ፡ ነው ከፍቅሩ ፡ ባለቤት ፡ ከሆነ ፡ ውሎዋችን በአንድነት ፡ ይገለጥ ፡ እውነት ፡ አምልኳችን በፍቅር ፡ አምልኳችን ስንበላም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንጠጣም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንገባም ፡ አንድ ፡ ላይ ስንወጣም ፡ አንድ ፡ ላይ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ዘምን ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ኖረናል ውስጥ ፡ ውስጡን ፡ ተባልተን ፡ ተለያይተናል ምን ፡ ያደርጋል ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን እምነት ፡ ቢሞላ ፡ ዕውቀት ፡ ቢከበኝ ልሳን ፡ መናገር ፡ ትንቢት ፡ ቢኖረኝ ሥጋዬን ፡ ለእሳት ፡ ብሰጥ ፡ ፈቅጄ ባልነፍግ፡ ለድሆች ፡ ያለኝን ፡ ከእጄ [1] ፍቅር ፡ የሌለው ፡ እልፍ ፡ ደግነት ጌታ ፡ የሌለበት ፡ መንፈሳዊነት ወዴት ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ከንቱ ፡ ጉዞ በሃሜት ፡ ታዝሎ ፡ በቂም ፡ ተይዞ ዞሮ ፡ ለማን ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ጥል ፡ ግርግር አቤል ፡ ከቃየል ፡ የማይሆን ፡ አጥር ጐራ ፡ ለይቶ ፡ ይቅር ፡ ማድሩ የእውነት ፡ ፍቅር ፡ ይግባ ፡ መንደሩ የባላንጣችን ፡ ደስታው ፡ ይደፍርስ በፍቅር ፡ ዘምተን ፡ ሰላም ፡ እንመልስ የቁርሾን ፡ ዘመን ፡ ይበቃ ፡ ብለነው መዘናጠሉ ፡ ነው ፡ ወዲያ ፡ እንጣለው ፍቅር ፡ ይበቀለው በረከት ፡ ደርሶ ፡ ደጅ ፡ አይመለስ የተወሰድው ፡ ክብርም ፡ ይመለስ ፍቱን ፡ መድሃኒት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ፈውሱ ለምድሪቱ ፡ ቀውስ ፡ ጥያቄ ፡ መልሱ ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን (፪x) ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን