Loading
Singer
በግራና ፡ በቀኜ ፡ ሆናችሁ ልታጠምዱኝ ፡ ያሰፈሰፋችሁ በሉ ፡ ስሙኝ ፡ እስቲ ፡ ልንገራችሁ በእኔ ፡ ዘንድ ፡ ደግሞ ፡ ምን ፡ ቀራችሁ አትጠጉኝ ፡ አትነካኩኝ ተለያየን ፡ እኔ ፡ የጌታ ፡ ነኝ በዓለም ፡ ብኖር ፡ አይደለሁ ፡ የዓለም መኖሪያዬ ፡ ለዘልዓለም በዚህች ፡ ምድር ፡ ፍጹም ፡ አይደለም በዚህች ፡ ዓለም ፡ ፍጹም ፡ አይደለም (፪x) አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ (አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ (አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ (አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ የአምላክ ፡ ምክር ፡ የልዑል ፡ ትምህርቱ የሰማሁት ፡ አዋጅ ፡ የመንግሥቱ ውስጤ ፡ ገብቶ ፡ ሰርፆ ፡ ልቦናዬ አጣብቆኛል ፡ ከውዱ ፡ ጌታዬ ጊዜም ፡ የለኝ ፡ ዓለም ፡ ምሰማሽ እረሳሁሽ ፡ አንቺም ፡ እኔን ፡ እርሺኝ በአምላኬ ፡ ዘንድ ፡ ተሰራልኝ ፡ ቤቴ ሰማያዊ ፡ ሆኗል ፡ ዜግነቴ (፭x) አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ (አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ (አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ (አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ በዚህ ፡ ምድር ፡ ቋሚ ፡ ነገር ፡ የለም ምስቅልቅል ፡ ነው ፡ ሲኖር ፡ በዚህ ፡ ዓለም የከበረ ፡ ነገ ፡ ይዋረዳል ያለቀሰ ፡ በተራው ፡ ይስቃል ግራ ፡ ገብቶት ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲሰጋ የማምለጫው ፡ መንገዱ ፡ ሲዘጋ ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬው የእንግድነት ፡ ኑሮ ፡ ጀምሬያለሁ አገር ፡ አለኝ ፡ ቤቴ ፡ በሰማይ ፡ ነው ተስፋ ፡ አለኝ ፡ ርስቴ ፡ በሰማይ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ (አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ (አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ (አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ የሰው ፡ ዕድሜ ፡ መች ፡ ከሰባው ፡ ያልፋል ቢበረታ ፡ ሰማንያ ፡ ይሆናል ጥቂት ፡ ታይቶ ፡ ኋላ ፡ እንደሚጠፋ እንፋሎት ፡ ነው ፡ የኛ ፡ መኖር ፡ ተስፋ እኔ ፡ ግን ፡ መች ፡ በምድር ፡ እቀራለሁ በሰማይ ፡ ቤት ፡ መኖሪያ ፡ አግኝቻለሁ ጌታ ፡ የግል ፡ አዳኜ ፡ ሆኖኛል በብርሃኑ ፡ ብርሃን ፡ ወጥቶልኛል የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ተሰጥቶኛል የፍርድ ፡ ቀን ፡ ለምን ፡ ያሰጋኛል (፪x) አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ (አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ (አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ (አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ