Loading
Singer
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ አንደመኖር በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ ከአንተ ፡ ጋር ፡ አንደመኖር እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ የለወጠው እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለን ፡ የህይወት ፡ ቃል ሌላ ፡ ስፍራ ፡ የትም ፡ ማላገኘው ብር ፡ የማይሰጠኝ ፡ ወርቅ ፡ የማይሰጠኝ የሕይወቴን ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠው የሁልጊዜ ፡ ነው ፡ የልቤ ፡ ሰላም ከመንፈስህ ፡ ከቃልህ ፡ የመነጨው በዚህ ፡ አለም ፡ ነገር ፡ የማይወሰን የእኔን ፡ ሕይወት ፡ የደስታ ፡ ያደረገው ብዙ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ ብዙ ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ በሕይወቴ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ስላለ ሸክም ፡ የከበደው ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣ ይረፍ ፡ ብለህ ፡ የጠራኸኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለ ፡ አንተ ፡ ሰጥቼ እፎይ ፡ ብዬ ፡ ተደላድዬ ፡ ምኖርብህ ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያለኝ ፡ ህብረት ማለት ፡ ለእኔ ፡ አለሜ ፡ ነው ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ያገኘሁበት ምክኒያቱ ፡ ነው ፡ የዘላለሜ ፡ የሰመረበት